+251118132191
contact@mint.gov.et
የሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገትን የሚያጎለብት የኢትዮጵያ ስታርታፕን ለመገንባት የትብብር ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ገለፁ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ የስታርታፕ ስነ-ምህዳርን ለመገንባት ቀደም ብሎ የተደረግውን የመግባቢያ ስምምነት ወደ ስራ ለማስገባት የፊርማ ስነስርዓት ተካሂዷል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የጃፓን ዓለም የትብብር ኤጀንሲ(ጃይካ) ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ላሉ ሀገራት ልምድ በማካፈል፣ የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግና ምቹ የስታርታፕ ስነ-ምህዳር ለመፍጠር በትብብር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን መስራቱን ገልፀዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው በሀገራች የስታርታፕ ስነ-ምህዳር ግንባታ ላይ የሚሰራው ፕሮጀክት በፈረንጆች አቆጣጠር ከነሃሴ 2025 እስክ 2028 ለሦስት አመት እንደሚቆይ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ የስታርታፕ ስነ-ምህዳር ግንባታ ላይ ለምታደርገው ጥረት ትብብሩ የላቀ ሚና አለው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የጃፓን መንግስት ባለፍት አመታት ለኢትዮጵያ የስታርታፕ የስነ- ምህዳር ግንባታ መጎልበትና ለስታርታፖች የተደረገው ድጋፍ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ገልፀዋል።
አክለውም ሚኒስቴር መ/ቤቱ ለፕሮጀክቱ ስኬት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ በመግለጽ፤ የጃፓን መንግስት ቀጣይ በሆን መልኩ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
የጃይካ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ከንሱኬ ኦሺማ (Kensuke Oshima)፤ የጃፓን መንግስት የስታርታፕ ምህዳርን ማጎልበት ላይ ቀጣይነት ያለው ልምድ የማካፈል እና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።
ይህ ትብብር በኢትዮጵያ ውስጥ የስታርታፕ ንግድ አካባቢ ፈጣሪነት፣ የሙያ እድገት እና የሥራ ዕድሎችን ለማሳደግ ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው የሚጠበቅ ሲሆን፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የረጅም ጊዜ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች