+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የሀገራዊ የስታርታፕ ዲጅታል ፕላትፎርም መዘጋጀት ለስታርታፕ ስነ-ምህዳር ግንባታ ቁልፍ ሚና እንዳለው ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ገለፁ።

በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስታርትአፕ ኢትዮጵያ የዲጅታል ፕላትፎርም (Startup Ethiopia Digital platform) ፕሮጀክት ልማት የመጀመሪያ የፍላጎት ትንተና ምዕራፍ ስራ ተጀምሯል።

ከኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (KOICA) ጋር በትብብር የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት በሀገር ደረጃ ለስታርታፖችና ስታርትአፕ ስነ-ምህዳር ገንቢዎች አገልግሎትና መረጃ ተደራሽ ለማድረግ፤ እንዲሁም የሀገሪቱን ስታርታፕ ስነ-ምህዳር ግንባታ ለማጎልበት የሚያስችል የዲጅታል ፕላትፎርም ለመዘርጋት ያለመ ነው፡፡

የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የስታርትአፕ ኢትዮጵያ ዲጅታል ፕላትፎርም (Startup Ethiopia digital platform) ልማት ፕሮጀክት በረቂቅ ስታርታፕ አዋጁ በተቀመጠው አግባብ የሚዘጋጅ ሲሆን ይህም ከህግ የማርቀቅ ሂድቱ ጋር ጎን ለጎን መተግበር መጀመሩ አዋጁን በፍጥነት ወደ ተግባር የሚያሽጋግር አቅም ይፈጥራል ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ለስታርታፖች ምቹ ስነምህዳር በመፍጠር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚኖራቸውን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ የገለጹ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በሄደው ዲጂታል ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት ለዘርፉ ምቹ አስራሮችንና ግብአቶችን መፍጠር አሰፈላጊ እንደሚሆን አንስተዋል።

የኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ የፕሮጀክት ቡድን መሪ ሚስተር ዩን ስለ ፕሮጀክቱ ያሉ ልምዶችንና የተጀመሩ ስራዎችን ያቀረቡ ሲሆን ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በፈጠራ መር የኢኮኖሚ እድገት ላይ ለምታደርገው ጉዞ ትልቅ ምዕራፍ እንደሚሆን በውይይቱ ተገልጿል።

ለስታርትአፕ ምቹ ስነ-ምህዳር ለመገንባት የአስራር ስርዓት የመዘርጋት ስራ እየተከናወነ ሲሆን ረቂቅ አዋጅ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና አጋር አካላት ተዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው አካላት ቀርቦ ግብዓት በማሰጠት ወደ ቀጣይ ሂድት መሸጋገሩ ተጠቁሟል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ