+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የሀገር በቀል እውቀቶችን ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ለመጠቀም በምርምርና በቴክኖሎጂ ሊደገፉ ይገባል ዶ/ር ባይሳ በዳዳ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ያሉ ሀገር በቀል ዕውቀቶችና ቴክኖሎጂዎች ላይ ሲያካሂድ የቆየውን የዳሰሳ ጥናትና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ፖርታል ሰርቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር መከረ።

ሀገራችን ያላትን እምቅ የሀገር በቀል እውቀቶችንና ቴክኖሎጂዎችን በማዘመን የኢኮኖሚው እድገት ማሳለጫ አንድ ምዕራፍ አድርጎ ለመጠቀም ያለመ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ ሀገር በቀል ዕውቀቶችንና ቴክኖሎጂዎችን ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ለመጠቀም የሚያስችላት የአሰራር ስርዓት ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው ብለዋል።

የሀገር በቀል ዕውቀቶች በምርምርና በቴክኖሎጂ በመደገፍ ከውጪ የምናስመጣቸውን በማስቀረት እራሳችን ችለን ለሌሎች ለመትረፍ በሚያስችል ስነምህዳር ላይ በመደራጀትና በመተባበር ከሂደት ወጥተን ተግባርና ውጤት ላይ መሰራት እንዳለበት ገልፀዋል፡፡

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቴክኖሎጂ ልማትና ሽግግር መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተክለማሪያም ተሰማ የምርምር ድጋፍ የሚፈልጉ የሀገር በቀል ዕውቀቶች መረጃዎችን በማዘመን በሁሉም አለም ሀገራት እውቅና እንዲያገኙና ወደ ሀብት ተቀይረው ተጠቃሚነታቸው እንዲሰፋ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተዋል፡፡

አክለውም የሀገር በቀል እውቀቶች ናቸው ተብለው በምርምር የተረጋገጡና እውቅና ያገኙትን በፖርታል በማስቀመጥ ህብረተሰቡ ጋ ተደራሽ እንዲሆኑ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሀገር በቀል እውቀቶችንና ቴክኖሎጂዎችን ሀገር እንድትጠቀምበት አስፈላጊው ምቹ ስርዓት ሊገነባለት እንደሚገባ ተሳታፊዎች አንስተዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ