+251118132191
contact@mint.gov.et
የልማት አጋሮች በአባልነት የየያዘ የኢኖቬሽን፣የዲጅታል ኢኮኖሚ እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የጋራ ግብረሃይል ተቋቋመ
ግብረሃይል በኢትዮጵያ ውስጥ በዘርፋ የሚሠሩ የልማት አጋሮችን እና ሌሎች ተዋናዮችን የሚያካትት ሲሆን ከአገራዊው የልማት አጋሮች የመሠረተ ልማት ቡድን ስር በመሆን ዘርፍን የሚያግዝ ነው።
ፕሮግራሙ በፈጠራ፣ በዲጂታል ኢኮኖሚ እና አይሲቲ ዘርፍ ዙሪያ የልማት አጋሮች የስራ ቡድን (DPG) ጋር የተካሄደ ሲሆን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በጋራ አዘጋጅተውታል።
በኢትዮጵያ በፈጠራ፣ በምርምር እና በቴክኖሎጂ ሀገራዊ አቅምን ማሳደግ፣አጠቃቀሙን ለማሳደግ የዲጂታል ኢኮኖሚን ማዳበር እና ማስፋፋት፣በቴክኖሎጂ በተደገፉ ኢንዱስትሪዎች ምርታማነትን እና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፣ለፈጠራ እና ቴክኖሎጂ የአስተዳደር እና የቁጥጥር ማዕቀፎችን ማጠናከር የሚያስችሉ ስራዎች በተካሄደው ውይይት ተነስተውበታል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ድኤታ ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ የኢኖቬሽን፣ ዲጂታል ኢኮኖሚ እና አይሲቲ ሴክተር ጆይንት ግሩፕ (IDEI-SJWG) የሀገሪቱን ዲጂታል ኢኮኖሚ በማሳደግ ረገድ በመንግስት እና በልማት አጋሮች መካከል ያለውን ትብብር ለማሳደግ ሚናው የጎላ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘውም ኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመፍጠር በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑን ጠቅሰው የስራ እድል የሚፈጥር፣ ሀገራዊ ተወዳዳሪነትን የሚያጎለብት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን የሚደግፉ ፕሮግራሞችን በመቅረጽ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል ።
የተያዙ ግቦችን ለማሳካት በኢትዮጵያ መንግስት እና በልማት አጋሮቻችን መካከል ያለው ትብብር ወሳኝ ነው ያሉት ሚኒስትር ድኤታው ይህ ወርክሾፕ ቁልፍ የሆኑ የዘርፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ለፖሊሲ ውይይት፣ ቅንጅት እና የሀብት ማሰባሰብ ግልፅ እና ሁሉን አቀፍ መድረክ ሆኖ ያገለግላል ብለዋል።
በመድረኩ ላይ የልማት አጋሮች የስራ ቡድን(DPG) ሴክሬታሪያት ኃላፊ ፓው ብላንኬር የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ፣ፈጠራን እና የአይሲቲ ዘርፍ ስራዎችን ውጤታማ ድጋፍ ለማድረግ የስራ ቡድኑ በተደራጀ መልኩ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በተለይም ዲጂታል ሊትረሲን ለመፈጠር ሃገሪቱ ለዘርፉ በምቹ ስነ ምህዳር ግንባታ፣በፕላትፎርም ልማት፣በዲጂታል መሰረተ ልማት ዝርጋታ የጀመረችው ጥረት እንዲሳካ እቅዶችንና አፈጻጸማቸውን በመከታተል መስራት ይገባል ያሉ ሲሆን መንግስትም ቅድሚያ ሰጥቶ ሊሰር ይገባል ብለዋል።
ወርክሾፑ የለጋሾችን ግንኙነት ማቀላጠፍ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን ማስተዋወቅ እና የብሔራዊ ፖሊሲዎችን ከዓለም አቀፍ የልማት ጥረቶች ጋር ማጣጣሙን ያረጋግጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚ ዲጂታል ኢኮኖሚ እንድትሆን ለምታደርገው ጥረት የልማት አጋሮች ድጋፍ ወሳኝ ነው ያሉት ሚኒስትር ድኤታው መንግስት እና አጋሮቹ አሁን በመላ አገሪቱ ፈጠራን፣ ኢኮኖሚያዊ ብልጽግናን እና ዲጂታል ማካተትን የሚያበረታቱ ተጨባጭ ተነሳሽነቶችን በመተግበር ላይ በትኩረት እየሰሩ ነው ተብሏል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች