+251118132191
contact@mint.gov.et
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ስታርትአፕ አዋጅን በሙሉ ድምፅ አፀደቀ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባው፤ የስታርትአፕ አዋጅን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።
የፀደቀው አዋጅ “የኢትዮጵያ ስታርትአፕ አዋጅ” የሚል ስያሜ እንደተሰጠው፤ የሰው ሀብት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ይህ አዋጅ መፅደቁ እና ወደሥራ መግባቱ ኢትዮጵያ ያላትን ዕምቅ አቅም ተጠቅማ በቴክኖሎጂ እንድትበለፅግ ከማድረጉ በላይ፤ በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችላት መሆኑን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አስታውቀዋል።
አዋጁ በፌደራል፣ በክልሎች እና በከተማ አስተዳድሮች ተፈፃሚ ይሆናል ተብሏል።
አዋጁ ብዙ የፈጠራ ጥበብ ያላቸው ኢትዮጵያውያንን የሚያበረታታ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ሌሎች የሚያመርቷቸውን ሸቀጦች ከመግዛት ባለፈ ትውልድ ራሱ ፈጥሮ፣ ራሱ አምርቶ ራሱ አቅራቢ እንዲሆን የሚያስችልም ነው ተብሏል።
አዋጁ ከዚህ ባሻገር ስታርትአፖች በኢትዮጵያ ውስጥ ዕድገትና ልማትን ለማፋጠን ያላቸውን ቁልፍ ሚና እውቅና የሚሰጥ በመሆኑ፣ የሀገርን ዕምቅ አቅም ለመጠቀም እና የቴክኖሎጂ እመርታን ለማሳደግ አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሟል።
አዋጁ የስታርፖችን የስኬት ምጣኔ በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድግ፣ የፋይናንስ ድጋፍን የሚፈጥር እንዲሁም የሥራ ዕድልን የሚያሰፋ በመሆኑ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ ይጠበቃል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች