+251118132191
contact@mint.gov.et
የመጀመሪያው የአፍሪካ የባዮቴክኖሎጂ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
በኢትዮጵያ አዘጋጅነት የመጀመሪያው የአፍሪካ የባዮቴክኖሎጂ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የኢፌዲሪ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) በጉባኤው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የሀገርን ሁለንተናዊ እድገት እውን ለማድረግ ለሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸው መንግስት በባዮቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚሰሩ ስራዎችን ለመደገፍ ዝግጁ ነው ብለዋል። የጉባኤው ዓላማ ለአፍሪካ ሰፊ እና ዓለም አቀፋዊ የባዮቴክ ማህበረሰቦች መድረክ መፍጠር ሲሆን የአፍሪካ አህጉር እያጋጠሟት ያሉትን የባዮቴክኖሎጂ ሳይንሶች፣ እየተፈጠሩ ያሉ ጉዳዮች እና ተግዳሮቶች ላይ ለመወያየት ያስችላል ተብሏል። በተጨማሪም ተመራማሪዎችን እና ምሁራንን፣ የፕሮግራም አስተዳዳሪዎችን እንዲሁም ፖሊሲ አውጭዎችን ከመላው አፍሪካ በማሰባሰብ በባዮቴክኖሎጂ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ቁልፍ ውይይቶችን እንዲያደርጉም ይረዳል ነው የተባለው። በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የባዮቴክኖሎጂ ሳይንስ እና ሌሎች እድገቶች ዙሪያም እየተሰራ ያለውን ስራ ለማስተዋወቅ መድረጉ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። በጉባኤው ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ መሐመድ ሐሰን እና ሌሎችም ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ሶሳይቲ ከሌሎች መንግስታዊ አና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ጉባኤው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት ይካሄዳል።
ክቡር ዶ/ር ባይሳ በዳዳ
የምርምርና ኢኖቬሽን ልማት ሚኒስትር ዴኤታ
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች