+251118132191
contact@mint.gov.et
የምርምር ሥነ-ምግባር የሕግ ማዕቀፍ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሀገራችን በተበታተነ መልኩ እየተካሄዱ ላሉ የምርምር ስነ-ምግባር ሥራዎች ወጥ የሆነ ስርዓት እንዲኖር የሚያስችሉ የምርምር ስነ-ምግባር ረቂቅ ሰነዶች በማዘጋጀት ላይ ይገኛል።
ሚኒስቴሩ በሀገራዊ የምርምር ስነ-ምግባር መመሪያ(guideline) እና “Standard Operating Procedures” ዝግጅት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል፡፡
በምክክሩ መክፈቻ ላይ የሀገራዊ ምርምርና ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሀብታሙ አበራ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ልማት ግቦችን ለማሳካት ምርምር ወሳኝ ሚና እንዳለው እና ይህ ምርምር ውጤታማ እንዲሆን ደግሞ የምርምር ስነ-ምግባርን መስፈርት ያሟላ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋ።
የምርምር ስነ-ምግባር የምርምር ስራዎች በሰዎች፣ እንስሳትና በአካባቢ ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ መጠበቅ የሚያስችል ስርዓት መሆኑንም በሰፊው አብራርተዋል፡፡
ይህን የምርምር ስርዓት ለማጠናከርና ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ የምርምር ስነ-ምግባር ሰነዶች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አማካኝነት የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ እየተዘጋጁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በሰነድ ዝግጅቱ ላይ የተገኙት ባለሞያዎች በቀረቡ ሰነዶች ላይ ተጨማሪ ሙያዊ አስተያየቶችና ሀሳቦችን ሰጥተዋል፡፡
ሥነ-ምግባራዊ የምርምር ሥራዎች እንዲጎለብቱ ለማድረግና ማህበረሰቡ ከዘርፉ የሚኖረውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች