+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የሱፐርቪዥን ድጋፍ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ላይ ያሉ ክፍተቶችን ከማሳየት በላይ በጋራ ለመስራት ሰፊ እድል ይፈጥራል ዶ/ር በለጠ ሞላ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የፕላንና ልማት ሚኒሰቴር ከፍተኛ አመራሮች የአዲስ አበባ ከተማ የሱፐርቪዥን ድጋፍ ስራዎች በቂርቆስና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች የተሰሩ ቁልፍ የልማት ስራዎች ላይ ምልከታ አካሄዱ።

የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ሀገራች አሁን እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ምዕራፍ ላይ እንደሆነች ዘርፈ ብዙ የመጡ ለውጦች መሳያ ናቸው ብለዋል።

አዲስ አበባ ላይ ተግባራዊ የተደረጉ የዲጂታል ሪፎርም ተቋማቱን ከማዘመን አልፈው አገልግሎቱ በማሳለጥ የነበረውን ክፍተት ማከም እንደተቻለ የተዘረጋው ስርዓት ገላጭ መሆኑን አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ ሰፊ ወጣት የሆነ የሰው ሀይል ያላት ሀገር ናት ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ አሁን በአዲስ አበባ ላይ ያሉ ተሞክሮዎችን በመቀመር የወጣት ሀይሉን በማደራጀና ምቹ ሁኔታ በመፍጠሪ አትራፊ ማድረግ እንደሚቻል ገልፀዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የአዲስ አበባ ከተማ ላይ የተደረገው ሪፎርም ቀደም ሲል የነበሩትን ውስብስብ የሰራር ችግሮችን ከመፍታትም አልፎ ማሀበረሰቡን ተጠቃሚ አድርጓል ብለዋል።

ከሰራን መቀየር ይቻላል ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ በአዲስ አበባ ትላልቅ የልማት ስራዎች በመፈጠራቸው ዜጎች አምራች ሀይል እንዲሆኑ ማስቻሉን ገልፀዋል።

የሱፐርቪዥን ቡድኑ በቂርቆስና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የትምህርት ቤት ማስፋፊያዎች፣ የሌማት ቱርፋቶች፣ የተቀናጀ የከተማ ግብርና፣ የእሁድ ገበያ፣ የለሚ እንጀራ ፋብሪካ፣ ሰው ተኮር ልማቶች፣ የጋራ መናሪያ ቤቶች ግንባታ፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ የኮሪደር ልማቶችና ሌሎች ስራዎችን ተመልክቷል፡፡

 

 

 

 

 

 

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ