+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር ሥራዎች ለዘላቂ የልማት አቅጣጫ መፍትሔ ጠቋሚ መሆናቸው ተገለፀ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሳይንስ ግራንት ካውንሲል ተነሳሽነት እና በአፍሪካ የቴክኖሎጂ ጥናት ማዕከል (SGCI, ACTS–IDRC) የፋይናንስ ድጋፍ እየተከናወኑ ያሉ የጥናት ፕሮጀክቶችን ለመጎብኘት የማዕከሉ አመራሮች የተካተቱበት ልዑካን ቡድን በባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በመገኘት የተፈጠሩ ውጤቶችን በቅርብ ተመልክቶ እንደገና አረጋግጧል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ በኢንስቲትዩቱ እየተተገበሩ ያሉ ፕሮጀክቶች ከምርምር ደረጃ ተሻግረው የምርት ባለቤትነት መብት (product patent right) በማግኘት ወደ ኢንዱስትሪ ምርት ደረጃ መድረሳቸውንና ወደ ማምረት ሂደት መግባታቸውን በጉብኝቱ ወቅት አስረድተው።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሀገራዊ ምርምርና ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሀብታሙ አበራ በበኩላቸው በሳይንስ ግራንት ካውንሲሉ የፋይናንስ ድጋፍ እየተከናወኑ ያሉ የሳይንስ ጥናትና ምርምሮች አበረታች ውጤቶችን እያመጡ መሆናቸውን ገልጸው፣ ለሀገራዊ ሳይንሳዊ ልማት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ዘላቂነታቸው እንዲረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡

ከልዑካኑ ቡድን አባላት ዶ/ር ሴፋስ አድጄይ ሜንሳህ የጋና የአካባቢ፣ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር (MEST) ተወካይና የSGCI አሊያንስ ሊቀመንበር በጉብኝታቸው ባዩት የባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ምርምሮች ውጤታማነት እጅግ መበረታታቸውን ገልጸው፣ እነዚህ ተግባራት በአባል አገራት መካከል የእውቀት ሽግግርና የልምድ ልውውጥ እንዲጠናከር አዳዲስ ዕድሎችን እንደሚፈጥሩ አስረድተዋል፡፡

በተለይም በቦታው የተመለከቱ የምርምር ውጤቶች ናሙናዎች የቀላል የቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደቶችን ማሳደግ፣ የማክሮ አልጌ እሴት በመጨመር ምርትና ምርታማነትን ማረጋገጥ፣ ወደ ኮሜርሻላይዜሽን ማዋል እና ለተመራጭ የግብርና ዘር ማስፋፊያ የላቦራቶሪ አገልግሎቶች ምቹ ስነ-ምህዳር መፍጠር እንደሚያስችሉ ተጠቅሷል፡፡

በአገራት መካከል በባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ መስኮች የሚካሄዱ የትብብርና የቅንጅት ሳይንሳዊ ጥናቶች የዘላቂ ልማት አቅጣጫን በማሳየት መፍትሔ ጠቋሚ ሀሳቦችን እንደሚያመነጩ ተገልጿል፣ ይህም ሳይንስ በተግባር ወደ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲቀየር አስፈላጊ መሠረት እንደሚጥል ታውቋል፡፡

በአጠቃላይ ጉብኝቱ የሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር ውጤቶች ከላቦራቶሪ ወጥተው ወደ ኢንዱስትሪና ወደ ገበያ ሲገቡ ሀገራዊ ልማትን የሚያፋጥኑ መሆናቸውን በግልጽ ያሳየ ሲሆን፣ በቀጣይም በተጠናከረ አፍሪካዊ ትብብር እና በተቀናጀ የሳይንስ ድጋፍ ስርዓት ዘላቂ የልማት ራዕይን ማሳካት እንደሚቻል አስተማማኝ ምልክት ሆኗል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ