+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን (STI) ፖሊሲ ማስፈጸሚያ ስትራቴጂ ኃላፊነታችንን ለመወጣት የምንመራበት መንገድ ነው። ዶ/ር በለጠ ሞላ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን (STI) ፖሊሲ ማስፈጸሚያ ስትራቴጂ ስነድ ላይ ያዘጋጀው ወርክሾፕ በመካሄድ ላይ ነው።

በወርክሾፑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን (STI) ፖሊሲ ማስፈጸሚያ ስትራቴጂ ለሚኒስሮች፣ ለፌደራል ተቋማት ከፍተኛ ሃላፊዎች እንዲሁም ለክልል ቢሮ ሃላፊዎች እና ጥሪ ለተደረገላቸው አካላት ቀርቧል።

በዝግጅቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን (STI) ፖሊሲ ማስፈጸሚያ ስትራቴጂ ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሸጋገር ያለመ አገራዊ ስትራቴጂያችን ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ በስትራቴጂው ዝግጅት የተሳተፉ አካላትን አመስግነው የሳይንስና ቴክኖሎጂን ሃይል በመጠቀም የኢኮኖሚ እድገትን ለማራመድ፣የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪነታችንን ለማሳደግ የያዝነውን ርዕይ እውን ለማድረግ የዚህ ስትራቴጂ ወደ ስራ መግባት ወሳኝ ነው ብለዋል።

አያይዘውም ስትራቴጂው ሁሉንም ሴክተሮች የሚዳስስ መሆኑን አንስተው በዚህ ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን ወደፊት ያለው መንገድ ቁርጠኝነትን፣ ጽናትን እና የትብብር መንፈስን የሚጠይቅ መሆኑን በመጥቀስ ሴክተሮች ለዚህ የጋራ ራዕይ እንዴት አስተዋፅዖ ማድረግ እንደሚችሉ ዝግጁ እንዲሆኑ አንስተዋል።

በዝግጅቱ ላይ የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከል የኢትዮጵያ አስተባባሪ አቶ ሳሙኤል ፈቃደ ድርጅቱ ለስትራቴጂው ዝግጅት ድጋፍ ማድረቸውን ገልጸዋል

በዚህ መስል ስራዎች በሚደረግ የአጋርነት ተሳትፎ ፓሊሲ አውጪዎች፣ አስፈፃሚዎች፣ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ድጋፍ ሰጪ ተቋማት እንዲሁም የግል የንግድ ስራ ድጋፍ ሰጭዎች የተሻለ ስራ እንዲሰሩ ማስቻል ነው ብለዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ