+251118132191
contact@mint.gov.et
የስታርታፕ ረቂቅ አዋጅ ብዙ የፈጠራ ጥበብ ያላቸው ኢትዮጵያውያንን የሚያበረታታ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ገለጸ
የስታርታፕ ረቂቅ አዋጅ ብዙ የፈጠራ ጥበብ ያላቸው ኢትዮጵያውያንን የሚያበረታታ መሆኑን በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ነገሬ ሌንጮ (ዶ/ር) ገለፁ።
ከዚህም ባሻገር ሀገራችን ሌሎች የሚያመርቷቸውን ሸቀጦች ከመሸጥ ባለፈ ትውልድ ራሱ ፈጥሮ፣ ራሱ አምርቶ ራሱ እንዲያቀርብ ያስችለዋል ብለዋል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባቀረበው የስታርትአፕ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተለያዩ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ጋር የህዝብ ይፋዊ መድረክ በማዘጋጀት ውይይት አድርጓል።
ቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ነገሬ ሌንጮ (ዶ/ር) የዚህ መድረክ ዋነኛ ዓላማ አዋጁ ከፀደቀ በኋላ ለታለመለት አላማ ይውል ዘንድ ከሚመለከታቸው አካላት በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ ከወዲሁ ግብዓት እንዲገኝ ነው ብለዋል፡፡
በውይይቱም ቁልፍ ቁልፍ ሀሳቦች ተነስተዋል ያሉት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ለቀረቡት ጥያቄዎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል ተገቢው ምላሽና ማብራሪያ በመሰጠቱ የተሳካ መድረክ እንደነበር ገልፀዋል።
በውይይቱ መግቢያ ላይ የስታርትአፕ ረቂቅ አዋጅ ዓላማ፣ ትርጉም፣ ስለተፈጻሚነት ወሰን እንዲሁም የኮሚቴው ስልጣንና ተግባር፣ ለስታርትአፕ የሚሆኑ ግራንድ ፈንድና ዋስትና ፈንድ ሀሳብ፣ ግዴታ እና ክልከላዎችን በዝርዝር ቀርበዋል።
ከዚህ ቀደም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ኃላፊዎች ጋር አስረጂ መድረክ ተዘጋጅቶ ውይይት መደረጉ የሚታወቅ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለትም ከተለያዩ ተቋማት ጋር በረቂቅ አዋጁ መታየት አለባቸው በተባሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ ላይ ከተገኙ ተቋማት መካከልም ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዲሁም በስታርትአፕ ላይ ጥናትና ምርምሮችን ሲሰሩ የነበሩ ግለሰቦችም ይገኙበታል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ በርካታ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተዋል።
ከተነሱ ሀሳቦች መካከልም እንደግብርና ባሉ ብዙ መሻሻል በሚያስፈልጋቸው ዘርፎች ላይ በዋናነት ትኩረት ሰጥቶ መሰራት እንዳለበት፣ ከገቢ ግብር ጋር በተገናኘ የተጠቆሙት አቅጣጫዎች በድጋሚ ትኩረት ቢደረግባቸው፣ የማበረታቻ ሂደቱ ከኢንቨስትመንት ማበረታቻ ጋር ትንሽ ስለሚጣረስ በድጋሜ ቢታይ፣ ሴቶች እና አካል ጉዳተኞችን በልዩነት አልተመለከተምና ታሳቢ ቢደረግ የሚሉ እና ሌሎችም ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ይገኙበታል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች