+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የስነ ምግባር ግንባታ ላይ የሚውል አቅም የሀገር ግንባታ ላይ የሚደረገውን ጥረት ውጤታማ ለማድረግ ወሳኝ ነው።ፎዚያ አሚን ዶ/ር

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ስልጠናው ስነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሲሆን ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች እየተሰጠ ነው።

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፎዝያ አሚን የስነ ምግባር ግንባታ ላይ የሚውል አቅም የሀገር ግንባታ ላይ የሚደረገውን ጥረት ውጤታማ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

የሰነ-ምግባር ግንባታ ብልሹ አሰራርን ከምንጩ ለመከላከል የሚኖረው ሚና የጎላ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ፎዚያ አሚን ለተቋም ስኬታማነት የተቋሙን ማህበረሰብ በስነምግባር መገንባት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በዝግጅቱ ላይ የሰነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ተወካይ አቶ ሃረጎት አብርሃ ተቋማት ከስነ ምግባር ግንባታ ጎን ለጎን የሙስና መከላከል ስራን ለመስራት ለተቋማት የሙስና ተጋላጭነት ስጋት የሚፈጥሩ አሰራሮችን በጥናት መለየት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የሙስና መከላከል ስራን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ለመስራት ከሚንስቴር መስርያቤቱ ብዙ እንደሙጠብቁ በግልጽ የተጀመሩ የሙስና መከላከል ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የዘርፉ ተቋማት አመራሮች በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው አቶ ሃረጎት አንስተዋል።

ስነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን ስልጠና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ፣የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት፣የባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን እንዲሁም የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን አመራሮች እየወሰዱ ይገኛሉ።

 

 

 

 

 

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ