+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በተቋሙ አቅም የለሙ የፕላዝማ እና ራውተር ሲ ኤን ሲ ማሽኖችን ለአምስት ክልሎች አስረከበ።

የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) ዘመናዊ የፕላዝማ እና ራውተር ሲኤንሲ (የኮምፒውተር ቁጥር መቆጣጠሪያ) ማሽኖችን ለአምስት ክልሎች፡ አማራ፣ ትግራይ፣ ሲዳማ፣ አፋር እና ቤንሻንጉል-ጉሙዝ ክልሎች አስረክቧል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ ቴክሎጂዎችን እያለማ ለወጣቶች ስራ እድልን ለመፍጠር የሚያስችል የቴክኖሎጂ ሽግግሩ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸው በባለሙያዎች የለሙት ዘመናዊ ማሽኖች የሀገሪቱን የማኑፋክቸሪንግ እና የቴክኖሎጂ አቅምን ለማሳደግ ትልቅ ዕርምጃ ናቸው ብለዋል።

እነዚህ የ CNC ማሽኖች በተቀባይ ክልሎች ውስጥ የኢንዱስትሪ ልማትን፣ የሙያ ስልጠናን እና የምርምር ስራዎችን በመደገፍ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ከኢትዮጵያ ፍላጎት ጋር የሚጣጣም የሀገር ውስጥ ፈጠራን እና የቴክኖሎጂ አቅም እንዲኖር የሚበረታታ መሆኑን አንስተዋል።

ክልሎችም የተረከቧቸውን ማሽኖች ለወጣቶች የስራ እድል ከመጠር ባሻገር የቴክኖሎጂ ሽግግሩ እንዲሳልጡ አደራ በማለት ኢንስቲትዩቱ ክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

ማሽኞቹን የተረከቡ የክልል ሀላፊዎች በበኩላቸዉ ለየተደረገላቸዉ የማሽን ድጋፍ አመስግነው ማሽኑ ለወጣቶች ስራ እድል ለመፍጠር፣የአቅም ግንባታ ስራን ለመስራት እና ቴክኖሎጂውን ለማሸጋገር ከፍተኛ ሚና እንደሚጫዎት ገልጸዉ የኢንስቲትዩቱ ድግፍ በቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ስለ ማሽኖቹ አጠቃቀም ማኑዋል ተዘጋጅቶ ባለፉት ሁለት ቀናት ከክልሎቹ ለመጡት ባለሙያዎች ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱም ተገልጿል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ