+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የባዮ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ፈጠራና ምርምርን የሚያበረታታ ስነምህዳር በመፍጠር በባዮ ቴክኖሎጂ የሚደረጉ ምርምሮች እና የኢኖቬሽን ስራወችን ለማበረታታት ይረዳል።ዶ/ር ባይሳ በዳዳ

የኢኖቬሸንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የባዮ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል።

ስትራቴጂው ፈጠራና ምርምርን የሚያበረታታ ስነ-ምህዳር በመፍጠር በባዮ ቴክኖሎጂ በሚደረጉ ምርምሮች እና የኢኖቬሽን ስራወችን ለማበረታታት የሚያግዝ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ተናግረዋል።

የባዮ ኢኮኖሚ ሃገራቱ ያላቸውን ተፈጥሯዊ ታዳሽ ስነ ህይወታዊ ሀብቶችን ዘላቂነትን መሰረት ባደረገ እና ውጤታማ በሆነ መንገድ በመጠቀም የአካባቢያዊ ተጽእኖ በማያስከትል መልኩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አላማ ያደርገ መሆኑ ተነስቷል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የዘርፉ ባለሙያዎችን ባሳተፈዕ የስትራቴጂ ዝግጅቱ የግምገማ መድረክ ላይ ኢትዮጵያም የበለፀገ ስነ-ህይወታዊ እና የተለያዩ የተፈጥሮ ሀብቶች ባለቤት እንደመሆኗ እነዚህን ሃብቶች በመጠቀም ፤ ዘለቄታዊ ግብርናን በማስፋት ምርታማነትን በማጎልበት የምግብ ዋስትናን ለማረጋጋጥ ያስችላል ብለዋል።

ሚንስትር ድኤታው እያይዘውም ሃገራችን ያላትን ሰፊ የብዝሃ ህይወት ሃብት ፤ ሰፊ ሊሰራ የሚችል ወጣት የስራ ሃይል በፈጠራ እና በምርምር በማገዝ ተኪ ኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ ትኩረት ተደርጎ እንዲሰራ ያግዛል ብለዋል።

በአለም ላይ ከ 70 በላይ ሃገራት አፍሪካዊያንን ጨመሮ ባዮ ኢኮኖሚያቸው ላይ በሰፊው በመስራት ኢኮኖሚያዊ ና አካባቢያዊ ተጠቃሚነትን እያረጋገጡ እንደሚገኝ እንዲሁም በባዮ ኢኮኖሚ GDP 4 trilion (4.7 %) እንደሆና ይህም ወደ 30 trilion ሊያድግ እንደሚችል ይገመታል።

 

 

 

 

 

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ