+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሚኒስትር የኢትዮጵያን ዲጂታል ስኬት አድንቀዋል —የኢትዮ ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ወደ 7 ሚሊዮን አድጓል

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ክቡር መሐመድ ቢን አብደላ አል ገርጋዊ የ«5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሼቲቭ» ወደ 7 ሚሊዮን ተሳታፊዎች ማደጉን መግለጻቸውን የአቡዳቢ ኒውስ፣ ሐምሌ 6 ቀን 2026 እ.ኤ.አ. ዘግቧል።

በዘገባው ይህ ውሳኔ በሁለቱ ወዳጅ አገራት መካከል ያለው አጋርነት ያስመዘገበው ልዩ ውጤት የሚያንጸባርቅ መሆኑን ክቡር ሚኒስትር መሐመድ ቢን አብደላ አል ገርጋዊ መግለጻቸው

ተጠቁሟል።

ክቡር አል ገርጋዊ በመንግሥት ዘመናዊነት ዘርፍ የተመሠረተው የኢትዮጵያ–ኤምሬቶች አጋርነት፣ በሁለቱም አገራት አመራሮች ራዕይና መመሪያ ልዩ ውጤቶችን ማስመዝገቡን የገለጹ ሲሆን፤ ሁለቱ አገራትም በተለያዩ ዘርፎች የላቀ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳላቸውም አስታውሰዋል።

ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ያለው አጋርነት ዓለም አቀፍ ትብብር ማህበረሰቦችንና መንግሥታትን በማሳደግ፣ የሰው ሀብትን በማብቃት እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን በመደገፍ ረገድ ያለውን ተጨባጭ ተጽዕኖ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።

ኢኒሼቲቩ ከታቀደው ጊዜ ቀድሞ ግቡን በማሳካቱ ወደ ሰባት ሚሊዮን ተሳታፊዎች መስፋፋቱ፣ የአጋርነቱን ስኬትና ትርጉም ያለው አዎንታዊ ተጽዕኖ የሚያንጸባርቅ ከመሆኑም በላይ፣ ሁለቱ መንግሥታት ወጣቶችንና የነገ መሪዎችን ያማከሉ የጋራ ፕሮጀክቶችን ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት እንደሚያመላክት ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ይህ ስኬት ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ልዩ ውጤት መሆኑን ገልጸው፣ ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው የፓርላማ ውሎ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዟችን የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሸቲቭ ፕሮግራም ካስብነው በላይ አሳክተናል ማለታቸው ይታወቃል።

https://www.abudhabinews.net/.../uae-ethiopia-expand-5

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ