+251118132191
contact@mint.gov.et
የተገነቡት የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለመገንባት የሚጫዎቱት ሚና ከፍተኛ ነው። ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ በሁሉም የክልል ዋና ከተሞች እና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በተመረጡ የፌደራል ተቋማት ያስገነባቸውን 24 የስማርት የኮሚኒኬሽን ክፍሎች በዛሬው እለት በቨርችዋል ዘዴ በያሉበት አስመርቋል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሰው ሀብት ልማት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ የተገነቡት የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች የዲጂታል ኢኮኖሚውን በመገንባትና በሀገር ጉዳይ የሚወሰኑ ውሳኔዎችን በጋራ ለማድረግ የሚጫዎቱት ሚና ወሳኝ ነው ብለዋል።
እንዲህ አይነት መሰረተ ልማቶች በጤና በትምህርት፣በግብርና እና መሰል ዘርፎች ያሉ ተሞክሮዎችን ለማስፋፋት እና አዳዲስ እውቀቶችን በቀላሉ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚያግዙም ተናግረዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የስማርት ኮሚኒኬሽን ክፍሎች የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ አካል መሆናቸውን ጠቅሰው የመንግስት ተቋማት የዲጂታል ቴክኖሎጂን በተገቢው መንገድ እንዲጠቀሙ አስፍላጊ መሰረተ ልማቶችን ሟሟላት ከስትራቴጂው አላማ ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የመንግስት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ሚና በተቀላጠፈ መንገድ እንዲወጡ ለማስቻል የተገነቡት እነዚህ የኮሙኒኬሽን ክፍሎች የተሟሉ ዘማናዊ የመገልገያ ቁሳቁሶች እና ልዩ ልዩ የኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች የተገጠሙላቸው መሆናቸውንም ገልጸዋል።
የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች አላማ በተቋማት ውስጥ እና በተቋማት መካከል ያለውን የስራ ግኑኝነት የተሳለጠ በማድረግ፤ ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር፣ ለስራ ቅልጥፍና እና ለመልካም አስተዳደር አስተዋጽኦ ማድረግ ነው።
ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በተገነባው ማዕከል የተከበሩ ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ ፣በቤንሽንጉል ጉምዝ ክልል ዶ/ር በለጠ ሞላ ፣በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ፣ በጋምቤላ ክልል ዶ/ር ባይሳ በዳዳ እና ም/ርዕሰ መስተዳድሩ ዶ/ር ጋትሉዋክ ሮን ፣ በሶማሌ ክልል ዶ/ር ፎዚያ አሚን፣በአፋር ክልል ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ፣በፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታው ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሃን እንዲሁም በየ ማዕከላቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት 24 የኮሙኒኬሽን ክፍሎች ተመርቀው ለአግልግሎት ክፍት ሆነዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች