+251118132191
contact@mint.gov.et
የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ኢትዮጵያውያን በመተባበር ሲሰሩ የሚመጣው ውጤት ማሳያ ነው።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች የታላቁ ኢትዮጵ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ ዓመት“በኅብረት ችለናል!” በሚል መሪ ቃል አክብረዋል።
በዝግጅቱ ላይ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ኢትዮጵያውያን በመተባበር ሲሰሩ የሚመጣው ውጤት ማሳያ ነው ብለዋል።
ግድቡ በሁላችን ገንዘብ ተገንብቶ ለሁላችንም የሚውል ኢትዮጵያውያን አንድ የሚያደርግ በመሆኑ መላው ኢትዮጵያውያን ያሳተፈ በሁሉም ዘንድ እንደ ልጅ የሚታይ የጋራ ቋንቋ የሆነ ፕሮጀክት እንደሆነም አንስተዋል።
ለግድቡ እውን መሆን መላው ኢትዮጵያውያን ባለፉት ዓመታት በየደረጃው ላደረገት ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ሚኒስትር ድኤታው አለም አቀፍ መነጋገርያ የሆነውን ይህንን ፕሮጀክት ኢትዮጵያውያን በህብረት ማሳካት ችለናል ለዚህም ከፍ ያለ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለው ብለዋል።
ሚኒስትር ድኤታው በሕዳሴ ግድቡ ላይ የታየው ንቁ ተሳትፎ እና መተባበርን በሌሎች የልማት ዘርፎች በመድገብ የኢትዮጵያን እድገትና ብልጽግና ማምጣት አለብን ብለዋል።
በዝግጅቱ ላይ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አንተነህ ተስፋዬ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት አሁናዊ መረጃዎችን አቅርበው በሰራቱኞች ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
ግድቡ በዚህ ዘመን ያሉ ዜጎች አሻራ ነው ያሉት ሃላፊው በየደረጃው ያሉ ዜጎች ለግድቡ የመጨረሻ ድጋፋቸውን በማድረግ አሻራቸውን እንዲያጸኑ አንስተዋል።
በውይይቱ የሚኒስቴሩ ሰራተኞች ለህዳሴው ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት መጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጣ ያነሱ ሲሆን ስኬቱ ከሃገርም አልፍ የአፍሪካውያንን የጋራ ታሪክ የሆነ ድል በመሆኑ የዚህ ዘመን ትውልድ አሻራ ነው ብለዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች