+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የቴክኖሎጂ ዘርፍ ተዋናዮች በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና በዳታ ልየታ (Data Labeling) ላይ እውቀታቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ተገለጸ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሀገሪቱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ውስጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የዳታ ልየታ (Data Labeling) ዘርፎች ላይ ትኩረት ያደረገ የሥልጠና መርሃ ግብር አካሂዷል።

የሥልጠናውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የዳታ ልየታ (Data Labeling) በመንግስታዊና በግል ተቋማት የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል ቁልፍ ቴክኖሎጂዎች መሆናቸውን ገልፀዋል።

ቴክኖሎጂው ለሀገር ውስጥ ችግሮች መፍትሄ እንዲሰጥና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚሆንበትን ዕድል ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ አመላክተዋል።

በሀገሪቱ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ የሰው ኃይል ብቃት ማሳደግ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የዳታ ልየታ (Data Labeling) በቂ እውቀት መታጠቅ በዘርፉ ላይ ሰፊ የስራ እድሎችን ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መሰል ስልጠናዎችን በማስፋፋት፣ የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ምሰሶዎች ለማጠናከርና ዜጎች በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች ያገኙት እውቀት ወደ ተግባር በመለወጥ በሀገሪቱ የቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደት ውስጥ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ እንደሚያግዛቸው በመግለፅ መሰል መርሃ ግብሮች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባችው ጠቁመዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ