+251118132191
contact@mint.gov.et
የአለም አቀፍ ሮቦቲክስ ኦሎምፒያድ (World Robot Olympiad) ውድድር ላይ የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን የሚሰሯቸው ስራዎች የማህበረሰቡን ችግር የሚፍታ ሊሆን ይገባል።ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ከስቴምፓወር እና ከዩኤን ጋር የጋራ ውይይት አካሂዷል።
ውይይቱ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ (STEM) ለማጠናከር የሚያግዙ ስራዎችን በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው።
በውይይቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ የፈጠራ ስራዎችን ለመስራት ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ ላይ ትኩረት ተሰጥቶት መስራት ይገባዋል ብለዋል።
ያደጉ ሃገራት ተሞክሮ እንደሚያሳየው ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ (STEM) ላይ በትኩረት መስራታቸው ፈጣን እድገት ለማስመዝገብ እንዳገዛቸው እና እድገታቸው እንዳይገታ በልዩ ትኩረት እየሰሩ መሆኑን በማሳያነት ያነሱት ሚኒስትር ዲኤታው እንደሃገር ይህንን ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያን በመወከል በተለያዩ ቴክኖሎጂ ነክ ውድድሮች የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረት ውጤታማ ስራ እንዲሰራ እያስቻለ መሆኑን በውይይቱ ተገልጿል።
እንደ ወርልድ ሮቦቲክስ ባሉ ውድድሮች የሚቀርቡ ስራዎች ቀጥታ የማህበረሰቡን ፍላጎቶች እና ችግሮች የሚፈቱ እንዲሆኑ በቅርበት መስራት ተገቢ ነው።
በተለይም በቅርቡ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ይፋ የተደረገው የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ፕሮግራም የዚህ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ (STEM) ውጤት መሆኑ ተገልጿል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህ ዘርፍ እንዲጎለብት ፓሊሲና ስትራቴጂዎችን በማውጣት እየሰራ እንደሚገኝ ሚንስትር ዲኤታው በውይይቱ አንስተዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች