+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የአለም አቀፍ ኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ የሆነውን የቴክኖሎጂና የዲጂታል ዘርፍ ተዋናይ ለመሆን የ5 ሚልዮን የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና ሚናው የላቀ መሆኑን ዶ/ር በለጠ ሞላ ገለፁ።

የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀነሲ የ5 ሚልዮን ኮደርስ የወሰዱ ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ያሉ ሰራተኞች የምረቃ ፕሮግራም አካሄደ።

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ ለምታደርገው የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር አቅም ያለው የበቃና በክህሎት የዳበረ ሁሉንም መሸከም የሚችል የቴክኖሎጂ እውቀትን የታጠቀ ዜጋ ማፍራት ከቻልን የምንፈልገውን ውጤት በአጭር ጊዜ ማምጣት ያስችለናል ብለዋል።

ሀገራችን ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን ለማሳካት ሰፊ ስራዎች በመስራት መሰረት ተጥሏል ያሉት ሚኒስትሩ ለ5 ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የተዘጋጀውን የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ስልጠና እድል በመጠቀም በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ በዳታ ሳይንስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎች ራስን በማስታጠቅ ከሀገር አልፎ አለም አቀፍ የስራ እድሎችን መጋራት እንደሚያስችል አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ አቶ ሰለሞን አማረ የ5 ሚልዮን ኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የተቀመጠለትን ግብ እንዲያሳካና የዲጂታል ሰራዊት ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

ሀገራችን ያላት ከፍተኛ የወጣት ሀይል የተፈጠረውን እድል ሊጠቀምበት ይገባል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ያለውን የሰው ሀይል በማብቃት እና መሰረተ ልማትን በማሳለጥ ዜጎች ቤታቸው ሆነው አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉበት እድል መፈጠሩን ተናግረዋል።

በመጨረሻም አየተሰሩ ያሉ ሰራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እደሚቀጥሉ በመግለፅ ለ240 የኮዲግ ስልጠና ኮርሱን ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት የመስጠት ፕሮግራም ተካሂዷል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ