+251118132191
contact@mint.gov.et
የአረንጋዴ አሻራ በሀገር የኢኪኖሚ እድገት ውስጥ ሰዎች የተሻለ ኑሮ እና መልካም አከባቢ እንዲኖራቸው ከማድረግ አንፃር ከፍተኛ ሚና አለው። ዶ/ር በለጠ ሞላ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ከ2011 በጀት አመት ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘው የአረንጋዴ አሻራ መርሃ ግብር እና የበጎ አድራጎት ተግባራት ስር የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ ሰራተኞቹና ለተጠሪ ተቋማቱ እውቅና የመስጠት መርሃ ግብር አካሂዷል።
በፕሮግራሙ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ መንግስት በሚሰጠን አቅጣጫ መሰረት የአረንጋዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ የአቅመ ደካማ ቤቶችን እድሰት እና ግንባታ ስራ እና ሌሎች የበጎ አድራጎት ስራዎችን አጠናክረን እንስራለን ብለዋል።
የአረንጋዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ለማስቀጠል መትከል ብቻ ሳይሆን ማጽደቅና መንከባከብ፤ የአቅመ ደካማ ቤቶችንም ማፍረስ ብቻ ሳይሆን በተሻለ መገንባት አለብን ያሉት ሚኒስትሩ አረንጋዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በሀገር የኢኪኖሚ እድገት ውስጥ ሰዎች የተሻለ ኑሮ እና መልካም አከባቢ እንዲኖራቸው ከማድረግ አንፃር ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡
በመድረኩም በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2011 ዓ.ም የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ መርሀ ግብር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አስተዋፅኦ ምን ይመስል እንደነበር ቀርቧል።
በዚህም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ሀገራዊ እንቅስቃሴ የሚያሳይ የዲጂታል ፕላት ፎርም በማልማት የተከላ መርሀ ግብር መረጃ ፣ የአረንጋዴ አሻራ ትግበራ ቀጥታ እንቅስቃሴ፣ ለአረንጓዴ አሻራ ልማት የተለዩ ቦታዎችን ማመላከትና መሰል ስራዎች መስራት ተነስቷል።
በተጨማሪም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ተጠሪ ተቋማቱ ከ2011- 2017 በጀት አመት የአረንጋዴ አሻራ እና የክረምት በጎ አድራጎት ስራዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በዙሪያው ባሉ አከባቢዎች፣ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ በአለልቱ ከተማ፣ በመንዲዳ ከተማ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቴፒ፣ በኮምቦልቻ ከተማ ስራዎች ተከናውነዋል።
በአጠቃላይ 51 የአቅመ ደካማ ቤተሰቦች ቤት እድሳት እና ግንባታና ችግኝ ተከላ እንዲሁም የተማሪዎች የፅህፈት መሳሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ፣ የደም ልገሳ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡
ሁሉም ተጠሪ ተቋማት በበጎ አድራጎት እና በአረንጓዴ ልማት አሻራ ውጤታማ እንቅስቃሴ ያደረጉ ሲሆን በተለየ መልኩ 19 የአቅመ ደካማ ቤቶችን በመገንባትና ለአረንጓዴ ልማት መርሃ ግብር የጂኦስፓሻል መረጃዎችን በማቅረብና በማደራጀት የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ልዩ ተሸላሚ ሆኗል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች