+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት እንዲጠናከር እያደረገ የሚገኘው ድጋፍ ውጤታማ ነው።ዶ/ር በለጠ ሞላ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ክብርት ሶፊ ኢመስበርገር ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ለመደገፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ያተኮረ ነው።

በውይይቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በዲጂታል ኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማስረዳት የአውሮፓ ህብረት እያደረገ ለሚገኘው ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሚኒስትሩ ዲጂታል ክህሎትን ከማሳደግ አንጻር የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያን ኮደርስ ኢንሸቲቭን በማስጀመር እየሰራ መሆኑን ገልጸው የሀገሪቱን ዲጂታል ኢኮኖሚ ለማንቀሳቀስ የሚያስችል ክህሎት ያለው የሰው ሃይል ለመፍጠር ትልቅ ተስፋ እንደተጣለበት አንስተዋል።

የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት እንዲጠናከር እያደረገ የሚገኘው ድጋፍ ውጤታማ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ በተለይም የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ እውን ለማድረግ በህብረቱ ድጋፍ የተጀመሩ ስራዎች ውጤታቸው በሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ጎልቶ የታየ መሆኑን ተናግረዋል።

ሚንስትሩ እያይዘውም የአውሮፓ ህብረት ላደረገው ውጤታማ ድጋፍ አመስግነው መስል ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ወይዘሮ ሶፊ የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ትልልቅ ለውጦችን በማስተናገድ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

አምባሳደሯ በተለይም የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት፣የዲጂታል ንግድ ምዝገባ፣ፍቃድ አወጣጥ መሰል የኢ-ሰርቪስ አገልግሎቶች የሚበረታቱ ናቸው ብለዋል።

በቀጣይ የዲጂታል ኢኮኖሚውን ከማጠናከር በተጨማሪ ሌሎች ጉዳዮችን በማካተት በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ወይዘሮ ሶፊ ከኢመስበርገር ተናግረዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ