+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የአገር በቀል ምጣኔ ኃብት ማሻሻያው ለግሉ ዘርፍ ተሳትፎ በሰጠው ትኩረት በርካታ ሥራ ፈጣሪዎች ኢኮኖሚውን እየተቀላቀሉ ነው።ዶ/ር በለጠ ሞላ

በኢትዮጵያ ለስታርት አፕ ስነ ምህዳርን በማመቻቸት ተቋማዊና ሕጋዊ አሰራርን የሚዘረጋ ረቂቅ አዋጅ እና የቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭን መጀመርን ለማስተዋወቅ ያለመ ዝግጅት በሳይንስ ሙዝየም ተካሂዷል።

የረቂቅ አዋጁ ዓላማ ለስታርት አፕ ተቋማዊና ሕጋዊ ድጋፍን በመስጠት በኢትዮጵያ የዘርፉን እድገት ማሳለጥ ሲሆን የቲምቡክቱ ኢንሼቲቭ ለዚህ አላማ መሳካት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።

በዝግጅቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ መንግስት ለስታርታአፖ ሰነ ምህዳር ግንባታ የሰጠው ትኩረት እንደ ሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ አስተዳደራዊ እና ተቋማዊ ተግዳሮቶችን በታላቅ፣ የሀገር ውስጥ ማሻሻያዎች ለመፍታት ያለን ሀገራዊ አቅም ለጠቀም የሚያስችል ነው ብለዋል።

ይህ እቅድ የኢኮኖሚ ዕድገትን፣ ድህነትን ቅነሳን፣ ኢነርጂ ልማትን፣ ፈጠራን እና የሰው ሃብት ካፒታል ልማትን ጨምሮ ቁልፍ ዘርፎችን ያቀፈ መሆኑን አንስተዋል።

በተለይም የአገር በቀል ምጣኔ ኃብት ማሻሻያ ለግሉ ዘርፍ ተሳትፎ በሰጠው ትኩረት በርካታ ሥራ ፈጣሪዎች ኢኮኖሚውን እየተቀላቀሉ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የስታርትአፕ አዋጅ እና የቲምቡክቱ ኢንሼቲም ይህንን እንደሚያጠናክር ተናግረዋል።

ይህ ውጤት እንዲመጣ እና በተጀመረው መልኩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በማቋቋም፣የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ በማሻሻል፣ NEST እና ስታርትአፖ ኢትዮጵያን በማዘጋጀት እንዲሁም የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ካውንስል በመመስረት በርካታ ስራዎችን መስራቱን ሚኒስትሩ አንስተዋል።

በዝግጅቱ ላይ የገንዘብ ሚንስትር ድኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ባለፉት አመታት በተሰሩ ስራዎች በአጭር ግዜ በሀገር ውስጥ ትልቅ አቅም እንዳለ የታወቀበት እና ሀገራችን ለስታርትአፖች ምቹ እንድትሆን የመንግስት አቅጣጫ የተቀመጠበት እንዲሁም የዘርፉ ተዋንያን የጋራ ቅንጅት የተፈጠረበት መሆኑን ተናግረዋል።

የረቂቅ አዋጁ በስታርትአፕ ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታትና የፋይናንስ አቅርቦትን ለማመቻቸ እንደሚያግዝ ተጠቅሷል።

በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ ኢትዮጵያ በአለም እቅፍ ደረጃ የሚያወዳድር ያልተነካ ሃብት እንዳላት ያነሱት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል አፍሪካ በአለምአቀፍ ገበያዊ ተወዳዳሪ እንድትሆን ይህንን ሃብት በስትራቴጂ መምራትና መጠቀም አለብን ለዚህም የቲምቡክቱ ኢኒሻቲቭ አይነተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ዳይሬክተር ወ/ሮ አሁና ኢዚያኮንዋ ቲምበክቱ በአፍሪካውያን መካከል ያለውን የኢኖቬሽን ስነ-ምህዳርን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ አቅም የሚፈጥር ነው ያሉ ሲሆን ኢንሼቲቩ ውጤታማ እንዲሆን መንግስትን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፍ

የዘርፉ ተዋንያን በትብብር ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

በውይይቱ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣የልማት አጋር ድርጅቶች፣ስታርትአፖች፣የዘርፉ ባለሞያዎችና ሌሎች የዘርፉ ተዋናዮች ተገኝተዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ