+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የአፋር ክልል ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን ባሉበት ቦታና በተመቸ ጊዜ በመውሰድ ከወቅቱ ቴክኖሎጂ ጋር ሊጓዙ እንደሚገባ ተገለፀ።

የፌደራል ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ድጋፍና ክትትል ቡድን የክልሎችን የአምስት ወራት የኮደርስ ስልጠና የስራ አፈፃፀምን በተመለከተ ከሚመለከታቸው እካላት ጋር ተወያይቷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የድጋፍና ክትትል ቡድን መሪና በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የብሔራዊ ኤሌክትሮኒክስ፣ መንግስት ልማትና አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ታዘዘ፤ የክልሉ ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወጣቶች ላይ ይበልጥ ትኩረት በማድረግ ተግባሩን እንዲወጣ አሳስበዋል።

የክልሉ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን ባሉበት ቦታና በተመቸ ጊዜ በመውሰድ ከወቅቱ ቴክኖሎጂ ጋር ሊጓዙ እንደሚገባም መክረዋል።

''የስልጠና ተደራሽነትን አውን ለማድረግም በትምህርት ቤቶች ላይ ትኩረት መደረግ አለበት'' ያሉት ደግሞ በትምህርት ሚኒስቴር የአይ ሲ ቲና ዲጂታል ትምህርት ክፍል ስፔሻሊስትና የድጋፍና ክትትል ቡድኑ አባል አቶ ከድር ኡርጂ ናቸው።

በዚሁ መድረክ ላይ የተገኙት የክልሉ ኢትዮ ኮደርስ አፈፃፀም ስትሪንግ ኮሚቴ አባልና የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ ዓሊ በበኩላቸው ስልጠናው ቴክኖሎጂን በመጠቀም መወዳደር፣ መተግበርና መጠቀም የሚችሉ ወጣቶችን ለማፍራት ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።

በመሆኑም በስልጠናው ለሚመጣው ስኬት እውን መሆን ጠንክረን እንሰራለን'' ብለዋል።

ስልጠናው ስራቸውን በውጤታማነት ለማከናወን እንዳገዛቸው የገለጹት ደግሞ የመንግስት ስራተኛው ከድር ኢድሪስ ናቸው።

በክልሉ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ ለ1 ሺህ 300 ሰዎች መሰጠቱንም በመረጃው ተመላክቷል።

የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችለውን ነጻ የኦንላይን ሥልጠና እድሎች ተጠቃሚ ለመሆን https://ethiocoders.et/ በዚህ ሊንክ ላይ ይመዝገቡ።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ