+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢትዮጵያን አገራዊ አጀንዳዎች የሚደግፉ የጋራ የምርምር፣ የእውቀት ልውውጥ እና የአቅም ግንባታ ጥረቶችን ልንጠቀምባቸው ይገባል ዶ/ር ባይሳ በዳዳ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኦስትሪያ ከሚገኝው International Institute for Applied Systems Analysis (IIASA) ጋር የሀገሪቱን አንገብጋቢ ፈተናዎች ለመፍታት አዳዲስ መፍትሄዎችን፣ መሳሪያዎችን እና ሞዴሎችን በጋራ ለማዘጋጀት የሚያስችል የበይነ-መረብ ውይይት አካሂደዋል።

ምክክሩ በኢትዮጵያ እና በInternational Institute for Applied Systems Analysis (IAASA) መካከል ያለውን የኢትዮጵያን አገራዊ አጀንዳ የሚደግፉ የጋራ ምርምር፣ የዕውቀት ልውውጥ እና የአቅም ግንባታ ጥረቶች ተጨባጭ እድሎችን ለመለየት፣ ግንኙነት ለማጠናከርና ቀጣይ እርምጃዎችን ለማስቀመጥ ያለመ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ ኢትዮጵያ እድገትንና ልማትን ለማፋጠን በምርምር ላይ የተጠናከረ ኢንቨስትመንት እና አዳዲስ ፈጠራዎችን ወደ ገበያ ለማሸጋገር እየሰራች እንደሆነ ገልፀዋል።

ሀገራችን ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ክልላዊ አባል ሀገራት ንቁ ተሳታፊ ነች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የኢትዮጵያ የአስር አመት የልማት እቅድ (2021-2030) እና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎቹ ሳይንስ፣ ፈጠራ እና ቴክኖሎጂ የዘላቂ ልማት ወሳኝ አንቀሳቃሾች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሀገራዊ የምርምር ልማት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሀብታሙ አበራ ሀገራዊ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ግብርና እና የምግብ ስርዓት፣ ዘላቂነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ጤና፣ ደህንነት፣ ስነ-ምህዳር አገልግሎቶች፣ ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ መፍትሄዎች እና የቆሻሻ አያያዝ መሆናቸውን አንስተዋል።

አክለውም ምርምር እና ልማት (R&D) በዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምር ማዕከላት እና ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ምርምር እና ልማትን ማጠናከር እና በSTEM (ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ) መስኮች የሰለጠነ የሰው ኃይል መገንባት ላይ በጋራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

International Institute for Applied Systems Analysis (IIASA) ምክትል ዋና ዳይሬክተር ካረን ሊፕስ, ከአገሪቱ ልዩ ፈተናዎች ጋር የተጣጣሙ መሳሪያዎችን እና ሞዴሎችን ለማዘጋጀት እንደ የአየር ንብረት መቋቋም ሞዴሎች፣ የግብርና ምርታማነት መሣሪያዎች እና የኢነርጂ ማሻሻያ ማዕቀፎችን ለማዘጋጀት ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

በመጨርሻም የሀገሪቱን አንገብጋቢ ፈተናዎች ለመፍታት አዳዲስ መፍትሄዎችን፣ ውጤቶች፡ ለማምጣት የትብብር ቁልፍ ቦታዎችን በመለየት በቀጣይ የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱን ለመፈራረምና ወደ ስራ ለመግባት በጋራ እንደሚያዘጋጁ ተገልጿል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ