+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢትዮጵያ  መንግስት ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚመራበትን የዲጂታል መንግስት ስትራቴጂ እና የመንግሥት ኢንተርፕራይዝ አርክቴክቸር  የጥናት ሰነድ የማጠቃለያ ወርክሾፕ ተካሄደ።

ስትራቴጂው የዲጂታል መንግሥት የሚመራበትን እና የሚተገበርበትን ሂደት የሚተነትን፣ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጥ ሲሆን ለትግበራውም ስኬት ከታወቁ ደረጃዎችና ማዕቀፎች መካከል የኢንተርፕራይዝ አርኪቴክቸርን ያካተተ ነው። 
የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚው በማጎልበት ዓለም የደረሰበት እድገት ላይ ለመድረስ የዲጂታል ስትራቴጂው ወሳኝ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል።
የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማጎልበት የዲጂታል መሠረተ ልማት ዝርጋታዎችን ማስተባበር፣ የህዝብ አገልግሎቶችን ዲጂታይዜሽን እንዲመራ ማድረግ እና ዜጎቻችን ዘመኑን የዋጀ ክህሎት እንዲኖራቸው ማድረግን ስለሚጠይቅ በስትራቴጂ ላይ  የተመሰረተ ስራዎችን በመስራት የኢኮኖሚ ምህዋሩን በፍጥነት መዘወር ይጠበቅብናል ብለዋል።
በዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅም ላላት ኢትዮጵያ ሰነዱ ራዕይ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ አለም አቀፋዊ ምርጥ ልምዶችን ያካተተ እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዟችንን የሚመሩ ቁልፍ መርሆችን መሰረት ያደረገ የዲጂታል ስትራቴጂ መሆኑን አንስተዋል።
በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ተወካይ ትብብር ኃላፊ ሮቤርቶ ሺሊሮ ስትራቴጂው ኢትዮጵያ በዲጂታል፣ በሃይል እና በትራንስፖርት ዘርፎች ግልፅና ደህንነቱ የተጠበቀ አውታርን ለማሳደግ እና የጤና፣ የትምህርት እና የምርምር ስርዓቶችን በአለም ዙሪያ ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ የዲጂታል ዘርፉን በመሰረተ ልማት በማሻሻልና በማብቃት የምታደርገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑንም ገልፅዋል።
የኤሌክትሮኒክ መንግስት አገልግሎት ስትራቴጂ እና ኢንተርፕራይዝ አርክቴክቸር 2024- 2029 ሰነድ በቀጣይ ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ብሄራዊ ካውንስል፣  ቀርቦ እንደሚፀድቅና ወደ ሙከራ ትግበራ ይገባል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ