+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩንቨርስቲን በቴክኖሎጂ የማጠናከር ስራ እንሰራለን። ዶ/ር በለጠ ሞላ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮጵያ መከላከያ ዩንቨርስቲን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የዩንቨርሲቲው አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ፣ የምርምር ፕሮጀክት አፈጻጸም፣ የመማር ማስተማር ስራዎች፣ ለምርምር አገልግሎትና ለመማር ማስተማር የሚውሉ ቤተ-ሙከራዎች እንዲሁም በሌማት ቱርፋት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ተጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩንቨርስቲ በዘርፉ ከኢትዮጵያ አልፎ አፍሪካዊያንን በማስተማር ሀገራዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ላይ የሚገኝ ተቋም መሆኑን አይተናል ብለዋል።

ዩንቨርሲቲው ያለውን አቅም ለማጠናከር ከሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማት ጋር በትብብር መስራት እንደሚገባ ያነሱት ሚኒስትሩ በቀጣይ በስፔስ ቴክኖሎጂ፣ በባዮና ኢመርጂንግ ዘርፍ፣ በናኖ ቴክኖሎጂ፣ በሪቨርስ ኢንጂነሪንግና ሌሎች ተቋሙን በሚያግዙ ዘርፎች የጋራ እቅድና ፕሮጀክት በመንደፍ እንሰራለን ብለዋል።

ሁላችንም በየ ተሰማራንበት ዘርፍ ለሀገራችን ወታደሮች ነን ያሉት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩንቨርስቲን በዘመኑ ቴክኖሎጂ የማጠናከር ሃላፊነት የሁላችንም በመሆኑ ሀገራችን የሚያስፈልጋትን አቅም ለመፍጠር ከዩንቨርሲቲው ጋር በቅርበት እንሰራለን ብለዋል።

ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የላቀ ብቃት እንሰራለን

በሚል መሪ ቃል እየሰራ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ዩንቨርሲቲ ኮማንዳንት ብርጋዴር ጀነራል ከበደ ረጋሳ ዩንቨርሲቲው ያለውን የውስጥ አቅም በማስተባበር በርካታ የምርምር ስራዎችና የመማር ማስተማር ስራውን በመስራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ሀገራት ለምርምርና ልማት የሚሰጡት ትኩረት የምርምር ተቋማትን አቅም ከማጠናከር ባለፈ በሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ መሪ መሆን እንዲችሉ እንደሚያግዛቸው ከተሞክሮዎቻቸው ማየት እንደሚቻል የጠቀሱት ሃላፊው በሀገር ደረጃ ትልቅ አቅም ያለውን ይህ ዩንቨርስቲ በቴክኖሎጂ ከማጠናከር አንጻ ከሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማት ብዙ እንደሚጠብቁ አንስተዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በትምህርትን ስልጠና በምርምርና ልማት በማህበረሰብ አገልግሎትና ማማከር በዩንቨርሲቲው እና በስሩ በሚገኙ ኮሌጆች፣ 76 የአካዳሚክ ፕሮግራሞች በመስጠት ሀገራዊ ተልዕኮውን በመወጣት ላይ ነው።

በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ በተደረገው ውይይት በምርምርና የሰው ሃብት ልማት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና ልማት፣ በአለማቀፍ ግንኙነት፣ በአይሲቲ መሰረተ ልማት ግንባታንና ሌሎች የዘርፉ ስራዎች በጋራ ለመስራት በፍጥነት ወደ ተግባር እንዲገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ