+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢትዮጵያ ስታርታፕ ረቂቅ አዋጅ የስታርታፕና ኢኖቬሽን ምህዳርን በመፍጠር ለምህዳሩ መጎልበት አንኳር ጉዳዮችን ያካተተ ነው።
የኢትዮጵያ ስታርታፕ ረቂቅ አዋጅ፤ ከተለያዩ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት የረጅም ጊዜ ጥረት በኋላ አንኳር የሚባሉ የስታርታፖችን ፍላጎት ባማከለ መልኩ ተዘጋጅቶ በሚንስትሮች ምክርቤት 47ኛ መደበኛ ስብሰባ በሙሉ ድምጽ ተወስኖ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ተላለፈ፡፡
የኢትዮጵያ ስታርታፕ ረቂቅ አዋጅ የስታርታፕ እና ኢኖቬሽን ምህዳርን በመፍጠር ለምህዳሩ መጎልበት አንኳር ጉዳዮችን ያካተተ ሲሆን ስታርታፓች የሚመሰረቱበት፣የሚንቀሳቀሱበትና የሚያድጉበት እንዲሁም ቴክኖሎጂን ተግባራዊ በማድረግ አዳዲስ ምርቶችን የሚያመርቱበትና አገልግሎቶችን የሚሰጡበትን ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው።
በዘርፉ የሚስተዋሉ የፋይናንስ አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት እንዲያስችል ሆኖ የተዘጋጀው ይህ ረቂቅ አዋጁ በዋናንት የስታርታፕና የስታራፕ ምህዳር ገንቢዎች ትርጓሜና ስያሜን (designation)፤ ስያሜን ተከትሎ የፈንድ (Grant፣ Credit Grantee Scheme, and Fund of Fund)፤ ብሎም የተለያዩ ማትጊያ መንገዶችን እና የሙከራ ቁጥጥር ማዕቅፍ (Regulatory Sandbox) አንኳር ጉዳዮችን አካቷል፡፡
በቀጣይ የዚህ ረቂቅ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት መጽደቅን ተከትሎ ኢትዮጵያ ለዘርፉ የህግ ማዕቀፍን ከዘረጉ እንደ ደቡብ አፍሪካ፤ ግብጽ፤ ናይጄሪያ፤ ኬንያ፤ ሞሪሺየስ፤ ቱኒዚያና ሌሎች ውስን አገራት መካከል ትቀላቀላለች፡፡
በዚህም የሃገራችን የስታርታፕ ምህዳር የመጀመሪያ የእድገት ምዕራፍ ለማሳካት እና ከአለም አቀፍ ጋር የተናበበ የስታርታፕ ምህዳር ለመፍጠር ይህንንም ተከትሎ ቁልፍ ችግሮቻችን የሚፈቱ በቴክኖሎጂ የታገዙ ወይም ቴክኖሎጂ የሚፈጥሩ፤ ተመንዳጊና በተላያዩ ዘርፎች አዳዲስ መፍትሄዎችን በማቅረብ የገበያ መዋቅርን የሚለውጡ ስታርታፖች እንዲፈጠሩ የሚያሰችል መስረት ይጥላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም አለማቀፍና ሃገራዊ በስታርታፕና ኢኖቬሽን ላይ መዋለነዋያቸውን የሚያፈሱ ባላሀብቶችን የሚያሳትፍና ሃገራዊ የስታርታፕ ምህዳር ገንቢዎች በስፋት እንዲፈጠርሩም ምቹ መደላድል የሚፈጥር እንዲሆን ያደርጋል፡፡
ረቂቅ አዋጁን 47ኛው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ አይቶ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር፣የስታርትአፕ ተዋንያን እና ሌሎች የሚመለክታቸው ባለድርሻ አካላት በቀጣይ አዋጁ በህዝብ ተወካዮች ጸድቆ በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገባ የሚተጉ ሲሆን ጎን ለጎን ለአዋጁ መተግብር የሚያሰፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በማከናወን ላይ መሆኑ አያይዝን ለመግለጽ እንድወዳለን፡፡
በዚህም የሚመለከታችው የስታርርታፕ ምህዳር ተዋንያን በተለመደ ትብብርና ቅንጅት መሰራት እንዳለባቸው እንገልጻለን፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች