+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን በጥራት መንደር ውስጥ ባስገነባው ቢሮ በመግባት በይፋ ስራ ጀመረ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን በጥራት መንደር ባስገነባው ቢሮ በይፋ ስራ ጀመሯል።
በስራ ማስጀመርያ ዝግጅቱ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በሀገራችን የሚሰሩ የቴክኖሎጂ ቁጥጥር ስራዎች የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጡ ምቹ የስራ ከባቢ መፍጠር ትኩረት ተሰጥቶት እንደተሰራ ገልጸዋል።
በዚህም የቴክኖሎጂ ቁጥጥር ስራን የሚያግዙ ላቦራቶሪዎችን መገንባት፣ የቁጥጥር ስራውን በሚፈልገው ልክ ማደራጀትና የራዲዮአክቲቭ ዝቃጭ ማከማቻ ማዕከልን የማዘመን ስራዎች ዘርፉ የሚፈልጉውን የጥራት ደረጃ በመያዝ እንደተገነቡ ጠቅሰዋል።
የጥራት መንደር የኢትዮጵያን ከፍታን የሚያረጋግጥ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ሀገራችን በቴክኖሎጂው ዘርፍ እየመጣ ያለውን እድገት የማሳለጥና ደህንነቱ የተጠበቀ ስራን ስኬታማ ለማድረግ ሚናው የላቀ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎንፌ ግዙፍ ኢኮኖሚ ለሚገነባ ሀገር ተስፋውና በብርሃን ለተሞላ ህዝብ ሊያደርግ የሚችለው በአርቆ አስተዋይነት ጥራት ሊያረጋግጥና ሊያሳልጥ የሚችል የጥራት መንደር በመገንባት ለትውልድ የሚተርፍ ፀጋና ቱርፋትን አሻግሮ ማስቀመጥ ነው ብለዋል፡፡
የጥራት መንደሩ ተወዳዳሪ የማይገኝለት 20 ግዙፍ ህንፃዎች የተገነቡበት፣ 7.2 ሄክታር ላይ ያረፈ፣ 4 በሮች ያሉት፣ ከ150 በላይ ዘመናዊ ላብራቶሪዎች የተገጠመለት፣ የዘመኑን ተክኖሎጂ አሰራር ስርዓት የተላበሰ ሁሉም ነገር የተሟላለት ይሄ ቀረ የማይባልለት ስኬትን የሚያረጋግጥ መንደር መሆኑ አስገንዝበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ጌታቸው የተሳለጠ የቴክኖሎጂ ቁጥጥር አገልግሎትን ተግባራዊ ለማድረግ ተቋሙ ከምንጊዜውም በላይ በጥሩ ቁመና ላይ እንዲገኝ ገልፀው በዘርፉ የተያዘውን ራዕይን ለማሳካት የልህቀት ማዕከላትን በማስፋትና በመገንባት አጠቃላይ ሀገራዊ ጉዞን ወደ ተሻለ ኢኮኖሚ እድገት ለማሸጋገር ተግተን እንሰራለን ብለዋል።
በዝግጅቱ ላይ ለጥራት መንደር ግንባታና ስኬት ትልቁን ድርሻ ለነበራቸው ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ከፍተኛ ምስጋና የማቅረብና ህንጻው በውስጡ የያዘቸውን ዘመናዊ ግብዓቶች በቦታው የተገኙት ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተዟዙረው ጎብኝተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ያስገነባችው አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት መንደር በህዳር 2017 በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ መመረቁ ይታወሳል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች