+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ETEX 2025) የሁለተኛው ቀን ዝግጅት ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል።
አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን ለአፍሪካ ብልጽግና እና ትብብር” በሚል ጭብጥ እየተካሄደ ባለው “አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ለአፍሪካ” መርሃ ግብር አፍሪካ በሀገር በቀል የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የተመራ አካታች ብልጽግና በማምጣት የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ወደ አዲስ ዘመን እየተሻገረች መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አጽንኦት ሰጠተው አንሰተዋል።
ኢትዮጵያም በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና የክሂሎት ማበልጸጊያ ሥራዎች በአርዓያነት እየመራች መሆኑን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደ ኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲቲዮት፣ ዲጂታል መታወቂያ ብሎም “የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ” አይነት ፕሮግራሞቿ ኢትዮጵያ ሕልሞቿን ወደ ተጨባጭ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተግባራት መለወጥ ችላለች ብለዋል።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በ2030 ማንም ወደ ኋላ በማይቀርበት አኳኋን አፍሪካ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን በራሷ መልክ በሥነምግባር፣ በአካታችነት እና ዘላቂነት ቅርፅ ማስያዝ እንደሚኖርባት አስምረውበታል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች