+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢትዮጵያ ኒውክለር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከል ግንባታ የአዋጭነት ጥናት ሊሰራ ነው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሊጂ ሚኒስቴር ከሩሲያው ፌደሬሸን የመንግስት አቶሚክ ኢነርጂ ኮርፓሬሽን (ROSATOM)
ጋር የኢትዮጵያ ኒውክለር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከል ግንባታ አዋጪነት ጥናት የኮንትራት ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሊጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ እና በሩስያ የሩሳቶም ኮምፕሌክስ ኢንጂነሪንግ ፕሮጀክቶች ዳይሬክተር ሚስተር ቫዲም ሳቪሎቭ ፈርመውታል።
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የኢትዮጵያ መንግስትና የሩሲያ ፌደሬሽን የኒክሌር ኃይልን ለሰለማዊ ተግባር ለማዋል የሚያስችለውን ስምምነት የህዝብ ተወከዮች ምክር ቤት በአዋጅ 1230/2021 አጽድቆ ወደ ስራ መገባቱ አስታውሰዋል።
ሚኒስትሩ ይህን ስምምንት ተግባራዊ እንዲያደርግ ኃለፊነት የተሰጠው የኢኖቬሽንና ቴክሎኖጂ ሚኒስቴር ስራውን ለመስራት የሚያስችል የሰው ኃይል ልማት ፣ የሰነድ ቅድመ ዝግጅት እንዲሁም ስትራቴጂክ ሰነድ ልማት ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል፡፡
የኒኩሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከል ግንባታ አዋጪነት ጥናት ኮንትራት ስምምነት የኒውክለር ሀይልን ለሰላማዊ አላማ ለማዋል የተጀመረውን ስራ ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ሚኒስትሩ አንስተዋል።
በተለይም ስራው በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ካለው የሩሲያው ፌድሬሸን የመንግስት አቶሚክ ኢነርጂ ኮርፓሬሽን (ROSATOM) ጋር መሰራቱ ስራውን ውጤታማ ለማድረግ እንደሚረዳ ገልጸዋል።
በስምምነቱ ላይ በሩስያ የሩሳቶም ኮምፕሌክስ ኢንጂነሪንግ ፕሮጀክቶች ዳይሬክተር ሚስተር ቫዲም ሳቪሎቭ ፕሮጀክቱን ለታለመለት አላማ ለማዋል በተያዘለት ግዜ እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋል።
አያይዘውም ሀገራቸው የኒውክለር ሳይንስን ለሰላማዊ ተግባር በማዋል ያላት ልምድ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ከኢትዮጵያ ጋር መሰራቷን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኒውክለር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከል ግንባታ የአዋጨጭነት ጥናት የፊርማ ሰነ-ስርአት ላይ በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢቭግኒ ታሪኪን ተገኝተዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች