+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢትዮጵያ ኒውክለር ሳይንስ ማህበር 4ኛውን ዓመታዊ ጉባኤ አካሄደ፡፡
ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ኒውክለር ሳይንስ ሶሳይቲ “የኑክሌር ምርምር እና ትምህርት፡ አቅምን ማሳደግ በሚል መሪ ቃል 4ኛውን ዓመታዊ ጉባኤ አባላቱና የሚመለከታቸው በተገኙበት አካሂዷል፡፡
የጉባኤው ዓላማ የኒውክለር ሳይንስ ሶሳይቲው የወደፊት ብሩህ እሴት በማንፀባረቅ፣ በጋራ ፈጠራ ምርምሮችን ለመዳሰስና ምርጥ ተሞክሮዎችን መለዋወጥ እንዲሁም የጋራ አቅሞችን የሚያጎለብቱ ትርጉም ያላቸው ውይይቶች ለማድረግና ክህሎትን ለማዳበር ዕድል የሚፈጥር ነው፡፡
በጉባኤው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሣ በዳዳ እንደገለጹት ባለፉት ዓመታት በኒውክለር ሳይንስ ልማት ስነምህዳሩን ለማስፋት ንቁ፣ አዳጊ እንደሆነም የመንግስት ልዩ ትኩረት ሆኖ በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል፡፡
የሀገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ የኒውክለር ሳይንስ ዘርፍ የተሰማሩ ምሁራን ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የውሃ ጥራትን ለማረጋገጥ፣ የማይቆራረጥ ኃይል እንዲኖር፣ የግብርናውን ዘርፍ የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎች ለማዘመን፣ የጤና አገልግሎት አሰጠጥን ለማቃለል የኒውክለር ሳይንስ ጥናትና ምርምር ስራዎች እጅግ ወሳኝ መሆናቸውን አስገንዝበዋል፡፡
የኒውክለር ሳይንስ ባለሙያዎች የጋራ አቅሞችን በማጎልበት የጥናትና ምርምር ውጤቶችን ለማሻሻል፣ ለማሳደግና ለገበያ ለማቅረብ የሚደረጉ ጥናቶችን፣ የምርምርና ስርፀት ሥራዎችን የማበረታታት እና ወደ ተግባር ለማሸጋገር ለሚደረጉ ጥረቶች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ ያርጋል ብለዋል፡፡
እንደሀገር ትኩረት በተሰጣቸው የልማት መስኮች ላይ የሚከናወኑ የጥናትና ምርምር ውጤቶችን ለመንግስት በማቅረብ በቅንጅት መስራት እንዳለበት አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ጌታቸው የኒውክለር ሳይንስ ዘርፍ ለጤና አጠባበቅ፣ ለሃይል አቅርቦት፣ ለግብርና ለሌሎች የልማት ስራዎች ከጥናትና ምርምር እና ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም የበለጠ አስተማማኝ እንዲሆንና የሚገጥመንን ፈተና በጋራ ለመታደግ ሀገራችን የምትሻውን ኢኮኖሚ እንድታስመዘግብ ምቹ ሥነ-ምህዳር ለመፍጠር ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኒውክለር ሳይንስ ማህበር ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋፆ ለመፍጠር የሚያስችሉ የጥናት ምርምር ሥራዎች ለማከናወኝ የጋራ በማድረግ ዓመታዊ ጉባዬውን አጠናቋል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች