+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢትዮጵያ አለምቀፍ ስታርታፕ ዳታ ሃብ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ፣ Systemic Innovation, እንዲሁም GrowthAfrica ከ Dealroom.co ጋር በመተባበር በመረጃ ላይ የተመሰረተ ግንዛቤን ለመፍጠር እና አለምአቀፍ ደረጃን ለማሳደግ የተነደፈውን ለውጥ የሚያመጣ፣ አለማቀፍ ተደራሽነት ያለው የመረጃ ቋት በይፋ ስራ አስጀምሯል።

መድረኩ የከፈቱት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፋዊ ተደራሽነትን በማሳደግ ተዓማኒነትን ያለው መረጃ እንዲያጎለበትና የሀገራችንን ከአለም አቀፉ ስታርታፕ ስነምህዳር ጋር በማስተሳሰር በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ በማውጣት እና የስነ-ምህዳር ልማትን በመደገፍ ረገድ ጉልህ ሚና ያለው መሆኑ ገልጸዋል፡፡

የእዚህ ዳታ ሀብት ጠቀሜታ፤ ተደራሽነትን በማሳደግ አለማቀፍ ግንኙነቶችን የሚያጠናክር ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ስታርታፕ ስነ-ምህዳር ውስጥ ግልፅነትን የሚያሳደግና፣ የሀገር ውስጥ እና የአለምአቀፍ ስታርታፕ ስነ ምህዳር ዋና ተጫዋቾችን የሚያገናኝ ፕላትፎርም ነው ብለዋል።

ዳታው ፈጣን እድገት ካለው የኢትዮጵያ ገጽታ ጋር የተናበበ ሲሆን፣ ይህ መድረክ በሴክተሮች ውስጥ ያሉ ጅምር ስራዎችን በአሁናዊና አጠቃላይ እይታን በመስጠት ስታርታፖች፣ ባለሀብቶች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ተመራማሪዎች የተሻለ እና የበለጠ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ መስጠት እንደሚያስችል አስገንዝበዋል።

አክለውም አለምአቀፍ የቬንቸር ኢንቨስተሮችና አክስለሬተሮች ተሳትፎ እና ስርጭት አዝማሚያዎችን እንዲመዘኑ ማስቻሉን አንስተዋል፡፡

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢኖቬሽን ልማት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰላምሁን አደፍርስ የአንድ ሀገር ስታርታፕ ሥነ-ምህዳር ስኬት የሚለካው ከዓለም አቀፋዊ የኢኖቬሽን፣ ቢዝነስና እውቀት ስነ-ምህዳር ጋር ለማዋሃድ ባለው አቅም ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የዳታ ሀቡ የኢትዩጲያን የኢኖቬሽንና የስታርታፕ ሥነ-ምህዳር ተዋናዮችን ከዓለም አቀፋዊ ሥነ-ምህዳር ጋር በማጣመር ለዚህ ውህደት አስተዋፅዖ ማድረግ ላይ ከመነሻው አልሞ የተነሳ መሆኑን ጠቁመዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ