+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ከኢጣሊያኑ ማይንድ (MIND) ኩባንያ ጋር በትብብር ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ የስራ ሀላፊዎች ከኢጣሊያኑ ማይንድ (Milan INnovation District) ኩባንያ ተቋማዊና ኢንተርናሽናል ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር፡ ጋር በትብብር ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ መክረዋል።

የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ አህመድ ኢትዮጵያ አፅንኦት ሰጥታ በምትሰራው ዘርፍ ላይ ትኩረቱን ካደረገው ከኢጣሊያኑ ሚንድ ግዙፍና ብዙ አለም አቀፍ አጋር ካለው ኩባንያ ጋር የሚደረግ የትብብር ስራዎችን በአጭር ጊዜ ወደ ስራ ለማስገባት እንሰራለን ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት ያላት ፍላጎት ከፍተኛ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው አለምን በኢካኖሚ ያበለፀገውን ቴክኖሎጂ ከመጠቀም አልፎ ፈጣሪና ባለቤት ለመሆን ከተለያዩ ሀገራት ጋር በትብብር የሚሰሩ ስራዎች ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል።

የኢጣሊያኑ ማይንድ ኩባንያ ኩባንያ ተቋማዊና ኢንተርናሽናል ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አልቤርቶ ሚኖ ኩባንያቸው ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።

ኩባንያቸው ከተለያዩ 9 አለም አቀፍ ሀገራት ጋር በትብብር እየሰራ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ከኢትዮጵያ ጋር በቴክኖሎጂ፣ በሰው ሀይል ግንባታ፣ በስታርታፕ፣ በምርምርና በሌሎች ዘርፎች ላይ በትብብር ለመስራት እንደሚፈልጉ ጠቁመዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ