+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ እና ውጥኖች ላይ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽንና አውደ ጥናት በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም በክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሰገን ጥሩነህን ተከፍቷል

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና በኢትዮ ቴሌኮም የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ እና ውጥኖች ኤግዚቢሽንና አውደ ጥናት በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ነው።

ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሰገን ጥሩነህ መንግስት ሁሉም ኢትዮጵያውያን በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ እኩል ተሳትፎ ማድረግ የሚያስችላቸውን የዲጂታል መሰረተ ልማት በፍትሃዊነት ተደራሽ መሆንን የዲጂታል ኢኮኖሚው እድገት አስፈላጊ የሆኑ የህግ እና የአሰራር ማዕቀፎች መነደፋቸውን እና ስራ ላይ መዋላቸውን እንዲሁም ዜጎች መሰረታዊ የዲጂታል እውቀት እና ክህሎት ማግኘት መቻላቸውን ማረጋገጥ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ሀገራችን እንደ ሌሎች ሀገራት ፤ ዕድሎቹን ለመጠቀም እና ፈተናዎቹን ለማለፍ በርካታ ጥረቶችን እያደረገች ትገኛለች ያሉት ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የስትራቴጂዎቹ ትግበራም የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል፣ የንግድ አሰራርን በማዘመን እና የበለጠ አሳታፊ እና የበለፀገ ማህበረሰብ በመፍጠር ረገድ የሚኖራቸዉ ሚና ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ሀገራችን በዚህ ፈጣን እና ተለዋዋጭ ዘመን ውስጥ እድገቷን ለማረጋገጥ እንድትችል ኢኖቬሽንን ማስፋፋት፣ የዜጎችን ዲጂታል እውቀት እና ክህሎት ማሳደግ ፣ የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን ማልማት እና ሀገራዊ የቴክኖሎጂ አቅም እንዲጎለብት የሚያስችል ስነ-ምህዳር መገንባት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የዲጂታል ቴክኖሎጂው እድገት ዓለማችንን ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየቀየራት ይገኛል ያሉት ሚኒስትሩ ከሁሉም በላይ ግን ዘመኑ የሚፈልጋቸውን አመለካከቶች ማለትም ትብብር፣ ቅንጅት፣ ማካፈል፣ ቴክኖሎጂን መቀበል እና ቀጣይነት ያለው መሻሻል ማድረግ የመሳሰሉ አመለካከቶችን መላበስ እና በስራ መተርጎም እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ ፈጠራዎች እንዲስፋፉ ለማድረግ እና ሁሉንም ያካተተ ዲጂታል ማህበረሰብ ለመፍጠር የተሰጠውን ሃላፊነት ለመወጣት የዘርፉን የአሰራር ስአት ምቹ ለማድረግ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ካውንስሉ ውስጥ በትጋት እና በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ እና ውጥኖች ላይ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽንና አውደ ጥናት ላይ የክልል እና የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የፌዴራል እና የክልል ተቋማት ተጠሪዎች ፣ የኢንፎርሜሽን እና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ኃላፊዎች እና የዩኒቨርሲቲ ሙሁራን ተገኝተውበታል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ