+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ አይ ቲ ፓርክ እና Rcndc አማካሪ ድርጅት በጋራ የሚያዘጋጁት ፊውቸር ቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2025 በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በመጪው ኅዳር ወር በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል የሚካሄደውን ኤክስፖ በማስመልከት አዘጋጆቹ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው የቴክኖሎጂ ኤክስፖው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ስኬቶችን ፣የመሰረተ ልማትና የስነምህዳር ግንባታ ስራዎችን እንዲሁም በአይ ቲ ፓርክ የተገነቡና በግንባታ ሂደት የሚገኙ የቴክኖሎጂና ፈጠራ ልማት ስራዎችን ለማስተዋወቅ እና አለማቀፍ የቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንት እና አጋርነት ለመሳብ እንደሚያግዝ ተገልጿል።

በዝግጅቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሙሉቀን ቀሬ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የዲጂታል ኢኮኖሚ ተወዳዳሪነት ማሳደግ የሚያስችል አቅም ተፈጥሯል ብለዋል።

ሚኒስትር ድኤታው አያይዘውም ዘርፉን ለኢንቨስትመንት ምቹ ለማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰው በኤክስፖው ላይ የቴክኖሎጂ ክህሎት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን፣ የግልና የመንግስት ኩባንያዎች የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባቸውም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር አቢዮት ባዩ ኤክስፖው በዘርፉ ያሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን በማስተዋወቅ ባለሃብቶችን ለመሳብ እንደሚያግዝ አመልክተዋል፡፡

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የተገኙ ውጤቶችን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚያስችል ግብዓት ለመሰብሰብና ቀጣዩን የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ለማስተዋወቅ ዕድል ይፈጥራልም ብለዋል።

የኢትዮጵያ የአይ ቲ ፓርክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሔኖክ አሕመድ ፓርኩ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚጠበቅበትን ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ኤክስፖው በአይ ቲ ፓርክ የተገነቡና በግንባታ ሂደት የሚገኙ የቴክኖሎጂና ፈጠራ ልማት ስራዎችን ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ እንደሚሆን ተናግረዋል ።

በመግለጫው በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የተመዘገቡ ስኬቶች ፣የዘርፉ ምቹ ስነ ምህዳር ግንባታ ስራዎች እንደሚቀርቡበትም ተጠቁሟል።

ኤክስፖው የመንግስትና የግል ቴክኖሎጂ ልማት አጋርነትን የሚያሳድግ መሆኑን የገለጹት የRcndc አማካሪ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሬድዋን አብዱ ዝግጅቱ የግሉ ዘርፍ አጋርነት እና ተሳትፎን የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።

መግለጫውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሙሉቀን ቀሬ፣ የኢትዮጵያ የአይ ቲ ፓርክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሔኖክ አሕመድ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪ አብዮት ባዩ (ዶ/ር) እና የRcndc አማካሪ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሬድዋን አብዱ በጋራ ሰጥተዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ