+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለኢፌደሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠናው በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ሌሎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፎች ያተኮረ ሲሆን የህግ አውጭዎች ስለ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች እና በልዩልዩ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ግንዛቤ ለማሳደግ ያለመ ነው።
የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዙርያ ብቁ መሆን ምርጫ ሳይሆን ግዴታ በመሆኑ ለዚህ ዝግጁ መሆን ይገባል ብለዋል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት በሀገር ውስጥ ከሀገር በቀል የምጣኔ ኃብት ተሃድሶ አጀንዳ፣ ከአስር ዓመቱ የልማት እቅድ እና ከተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦች እንዲሁም ከአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ የዲጂታል ስትራቴጂ ጋር በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን አስታውሰዋል።
አያይዘውም የዘርፉን የህግ ማዕቀፎች ከአለም አቀፍ የቴክኖሎጂ አዝማሚያዎች ጋር በማጣጣም ረገድ የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያጎላ የቴክኖሎጂ እውቀት ያለው አመራር በመፍጠር የሀገሪቱን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ በብቃት ለመምራት በሁሉም መስክ ዝግጁ መሆን እንደሚገባም ገልጸዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን ወደ ማገባደጃው ስናደርስ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የኢኮኖሚ መሰረትን በመጣል ያስገኘናቸውን ጉልህ እመርታዎች በማጠናከር ታላላቅ ግቦችን ሰንቀን ወደ "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" በታላቅ ራዕይ የመሸጋገር ጉዟችን ውጤታማ እንዲሆን የዘርፉን ግንዛቤ የማሳደግ ስራ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
የቴክኖሎጂ እድገቶችን ወደ ህግ አውጪ ማዕቀፎች በማዋሃድ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና በዲጂታል ዘመን እድሎችን ለመጠቀም እንዲሁም ዘርፉን የሚያሰራ የህግ ስርአት ለመዘርጋት አስፈላጊ መሆኑንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሰው ሀብት ልማት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በፍጥነት እያደገ የመጣውን የቴክኖሎጂ አለም በመረዳት በእውቀት እና በመረጃ ላይ የተመሰረተ የአሰራር ስርዓቶችን ፤ፖሊሲዎችንና አዋጆችን ለመቅረጽ በዘርፉ ያለንን ግንዛቤ ለማሳደግ በቀጣይም እንዲህ መሰል ስልጠናዎችን መስጠት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል።
ስልጠናውን የወሰዱ የምክርቤቱ ከፍተኛ አመራሮች በቴክኖሎጂው ዘርፍ የአለምን ነባራዊ ሁኔታ ተገንዝቦ ለመስራት የሚያግዝ ግንዛቤ እንዳገኙ ያነሱ ሲሆን በቀጣይ በእነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ሊፈጠሩ ይገባል ብለዋል።
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ሌሎች የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች የተሰጠውን ስልጠና የሰጡት የቴክኖሎጂ ባለሙያው አቶ ሰለሞን ሙሉጌታ ናቸው።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች