+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽንን መሰረት ካደረጉ የሙያ ማህበራት ጋር በሀገራዊ የምርምርና ልማት አሰራር ሥርዓት ዙርያ ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱ ላይ በሚኒስቴሩ የሀገራዊ ምርምር ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ / ሃብታሙ አበራ ምርምር፣የቴክኖሎጂ ሽግግርና ልማት ላይ በትኩረት መስራት በዘርፉ ተወዳዳሪ የሰው ሀይል ለማልማትና  በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት ፣ሳይንሳዊ መንገድን የተከተለ እና በማስረጃ የተደገፈ ውሳኔ ለመስጠት እንዲሁም የተለያዩ ፖሊሲዎችን እና ስትራቴጂዎችን ቀርጾ ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማት ሥራዎች የዓለማችን አንገብጋቢ ችግሮችን ለመፍታት ቁልፍ መሳሪያ በመሆናቸው 2030 ዘላቂ የልማት ግቦችን እንዲሁም የአፍሪካ  አጀንዳ 2063 ለማሳካት ወሳኝ ድርሻ እንዳላቸውም በመድረኩ ተነስቷል፡፡

የሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፓሊሲ የዘርፉን ስነ-ምህዳር ውጤታማ ለማድረግ በሚያስችል መልኩ መዘጋጀቱ የተገለጸ ሲሆን  ፖሊሲውን ውጤታማ ለማድረግ የበርካታ ባለ ድርሻ አካላትን ንቁ ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ የግሉ ዘርፍ የሙያ ማህበራት ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው በመገንዘብ ለውጤታማነቱ የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ተጠቁሟል፡፡

በመድረኩም ብሄራዊ የምርምርና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ