+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በ«ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030» ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሀን ማብራሪያ ሰጠ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ በ«ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030» ዙሪያ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ያዘለ ምላሽ ሰጥተዋል።

የ«ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025» ስትራቴጂ በስኬት መጠናቀቁ ለ«ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030» መሠረት መጣሉን ገልጸው፣ ለሀገራዊ ዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት በአካታችነት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የ«ዲጂታል 2030» ትሩፋት ተጠቃሚ እንዲሆን በተግባር እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን በስፋት አብራርተዋል።

ዲጂታል ሉዓላዊነቷን የጠበቀች፣ በፈጠራና ቴክኖሎጂ የተመሠረተች ኢትዮጵያን ለመፍጠር «ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030» ስትራቴጂ ሁለንተናዊ መንገድ መሆኑን ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው አክለዋል።

የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ማጎልበት ለዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ የክህሎት ልማት ሥራዎች በቀጣይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።

የ«ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030» ስትራቴጂ የሀገሪቱን የልማት አቅጣጫ በቴክኖሎጂ መሠረት ለመቀየር የታለመ ትልቅ ሀገራዊ እቅድ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በንቃት ማሳተፍ የስትራቴጂው ዋነኛ መርህ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከስትራቴጂው ቁልፍ ነጥቦች መካከል የዜጎች መረጃ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህንን ለማሳካት የተቋማት አቅም ማጠናከርና ሀገራዊ መረጃዎችን በሀገር ውስጥ መጠበቅ ላይ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

የስታርታፕ አዋጁ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የስታርታፕ ማዕከል ለማድረግ፣ የፈጠራ ሥራዎችን ለማበረታታትና የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል ጠንካራ መሠረት ያለው መሆኑን አንስተዋል።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ለስታርታፕ አስፈላጊ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ የዲጂታል ክህሎት አቅም መፍጠር መሆኑን በመግለጽ፣ ለ«ዲጂታል 2030» ስትራቴጂ ስኬት ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በማልማትና በመጠቀም ሀብት ፈጣሪ አምራች ስታርታፖችና የዲጂታል ክህሎት አቅም ያጎለበቱ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ እንደሚሆን ይጠበቃል ብለዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ