+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በተመረጡ መንግስታዊ ተቋም ያስገነባቸውን 24 የስማርት ኮሚኒኬሽን ክፍሎች ግንባታ ፕሮጀክት ማጠናቀቂያ ፕሮግራም አካሄደ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በተመረጡ 10 የፌደራል ተቋማት፣ በ12 ክልሎችና በ2 የከተማ መስተዳደሮች ያስገነባውን የስማርት ኮሚኒኬሽን ክፍሎች ግንባታ ፕሮጀክት የተጠቃሚ ተቋማት የስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት የማጠናቀቂያ ፕሮግራም አካሂዷል፡፡

ፕሮግራሙ የስማርት ኮሚኒኬሽን ክፍሎች የተገነቡበት አላማ ተግባራዊነት ላይ ለመምከር፣ በግንባታው ሂደት ላይ የተገኙ ተሞክሮዎችን ለመቀመርና ለቀጣይ በግብዓትነት ለመጠቀም እና ለፕሮጄክቱ መሳካት አስተዋፅኦ ላበረከቱ ምስጋና ለማቅረብ ያለመ ነው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ተደራሽ የሆነ የዲጂታል ስርዓት በመገንባት የማህበረሰቡን አገልግሎት ለማዘመን ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አስገንዝበዋል፡፡

የዲጂታል ዘርፉን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ ፍላጎትና ቅንጅት ወሳኝ ሚና አለው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ሁሉም ተቋማት ወደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመግባት ተገልጋዮች ያለምንም እንግልት፣ ገንዘባቸውንና ጊዜያቸውን ቆጥበው ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአይሲቲ መሠረተ ልማት ግንባታና አስተዳደር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ዮናስ ኃይሉ ተቋማት የዲጂታል ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ በትብብር ላይ የተመሰረተ መሰረተ ልማትን ለማሟላት ከሚሰሩ ስራዎች የስማርት ኮሚኒኬሽን ክፍሎች ግንባታ ፕሮጀክት አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የዲጂታል ስርዓቱን ለማስፋት የዘርፉ ተዋናይ ከሆኑት ተቋማት ጋር የተጠናከረ ግኑኝነት በመፍጠር ለስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች የስራ ላይ ስልጠናና በአጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና በመሰጠቱ ፕሮጀክቱን ስኬታማ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም ለፕሮጀክቱ ስኬት አስተዋፆ ላበረከቱ ባለሙያዎችና ተሳታፊዎች የምስጋና መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ