+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የኩባ አምባሳደር ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ እና በኢትዮጵያ የኩባ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሜይሊን ሱአሬዝ አልቫሬዝ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ የኢትዮጵያ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ክብርት ሸዊት ሻንካ እና የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ኤድዋርዶ ሮድሪግዝ ፓሪላ በስፖርት ልማት ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ ረጅም እድሜ ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ እና ኩባ ወዳጅነት በማጠናከር በሁለትዮሽ የጋራ ጉዳዮች ላይ በመስራት ዘላቂነት ያለው ግንኙነት ለመፍጠር ያለመ ነው።
ኢትዮጵያ ከኩባ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት በማጠናከር በቴክኖሎጂው ዘርፍ ላይ በትብብር በመስራት ውጤት ማስመዝገብ እንሚቻል የተገለጸ ሲሆን፤ የኩባ መንግስት በቴክኖሎጂው ዘርፍ ትልቅ ልምድ ያለው በመሆኑ ኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በምታደርገው ርብርብ ውስጥ የሚመጡ አጋር አካላትን ለስኬት ማሳለጫነት ልንጠቀምባቸው ይገባል ተብሏል።
በኢትዮጵያ የኩባ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሜይሊን ሱአሬዝ አልቫሬዝ ከኢትዮጵያ ጋር የነበረው የረጅም ጊዜ ታሪክ በማንሳት ቀጣይነት ያለው ግንኝነትን በማጠናከር በቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።
ስምምነቱን ወደ መሬት ለማውረድ የሚያስችል ግንኙነት በመፍጠርና በመወያየት ተቀራርበው በሌሎችም ዘርፎች ላይ እንደሚሰሩ በስምነቱ ወቅት አመላክተዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች