+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኮምቦልቻ ከተማ የገነባቸውን የአቅመደካማ ቤቶች አጠናቆ አስረከበ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በተለያዩ ክልሎች ከሚያደርገው የችግኝ ተከላና የአቅመ ደካማ ቤቶች እድሳት መርሃ ግብር ውስጥ በኮምቦልቻ ከተማ በአዲስ መልክ የገነባቸውን 7 የመኖሪያ ቤትች በማጠናቀቅ የከተማው ከፍተኛ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ለአቅመደካሞች ቁልፍ አስረከቡ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የሀገራችንን የኢኮኖሚ እድገት ለማጎልበት በምናደርገው ርብርብ ውስጥ የአቅመ ደካሞችን ህይወት የኑሮ ሁኔታ ሊደግፉ በሚችሉ ዘርፎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት ገልፀዋል።
የተሰሩት የአቅመ ደካሞች ቤቶችን ሰርተን ስናስረክብ ቀጣይ ሌሎች ከዚህ በላይ መስራት እንዳለብን አቅም ከመሆን ባሻገር ሌሎች ተቋማትና ባለሀብቶች እንዲህ ባሉ ዘርፍ ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ መነሻ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስገንዝበዋል።
የስራችን ውጤት የሚለካው ለዜጎቻችን ባደረግነው ተጨባጭ ውጤት ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ በክረምት ካከናወናቸው መርሀ ግብር ውስጥ የተጀመሩ የአቅመ ደካማ የቤቶች ግንባታ ስራዎች በዚህ መልኩ ተጠናቀው ውጤት ላይ ደርሰው ስናያቸው በሁላችንም ዘንድ ከፍተኛ እርካታን ይፈጥራሉ ብለዋል።
የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ ክቡር መሀመድ አሚን በአለም ላይ ብዙ ሀገሮች ጂዲፒያቸውን የሚያገኙት ከከተሞቻቸው ሲሆን ይህንን ውጤት ለማምጣት በሀገራችን በማደግ ላይ ያሉ የከተሞቻችንን ውስብስብ ችግሮች ለመፍታትና ደረጃቸውን ለማሳደግ ሁሉን ባሳተፈ መልኩ መሰራት እንዳለበት ገልፀዋል።
መንግስት ከተሞችን ለማሳደግ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ አየሰራበት ያለውን እቅድ ለማሳካት አሮጌ ቤቶችን እና ሌሎች ሰው ተኮር በሆኑ ልማቶች ላይ ከተለያዩ አካላት ጋር በትብብር እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
በክረምት መረሀ ግብር በተለያዩ ክልሎች እየተከናወኑ ያሉ የችግኝ ተከላ፣ መማር ላልቻሉ ተማሪዎች የቁሳቁስ ድጋፍ፣ የአቅመ ደካሞች ቤቶች እድሳትና በአዲስ መልክ ሰርቶ ከማስረከብ ባለፈ ከተሞችን በዲጂታል ለማዘመን የሚደረጉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተጠቁሟል። በዚሁም መሠረት የኮምቦልቻ ከተማ፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ተቋም፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኮሌጅ የኮምቦልቻ ከተማን የዲጂታል አድራሻ ስርአት ለማልማት የሶስትዮሽ ስምምነት የፊርማ ስነስርአትም የተካሄደ ሲሆን በጂአይኤስ እንዲሁም በማዳበሪያ አዘገጃጀት ስልጠና ለወሰዱ ወጣቶች የሰርተፊኬት ሽልማት ተሰጥቷል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች