+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 አፈጻጸም ሂደት ለሰጠው አመራር ተመሰገነ፥
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቶ ተጠናቋል ሲሉ ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ማስጀመሪያ እለት ከክቡር የኢፌዴሪ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ጋር ባደረጉት ውይይት በተለይ ቀጣይ የሀገራችን የዲጅታል ሽግግር ጉዙ ምን እንደሚመስል በጥልቀትና በስፋት ምልከታቸውን ለህዝብ አካፍለዋል። በዚሁ እለትም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ መጀመሩን አብስረው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሰጠው አመራር ምስጋና አቅርበዋል።
አዲሱ የ2030 ዲጅታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት እንደሆኑ የገለጹት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ይህንንም ለማሳካት በጋራ መንቀሳቀስና ከፍ አድርጎ አቅዶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
እነዚህ ትልሞች እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ የሚከናወን ሲሆን፣ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል።
በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩም ናቸው ብለዋል።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፥ ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላን እንደ አገር በመደመር መንግስት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና በድጅታል ኢትዮጵያ 2025 አፈጻጸም ለሰጡት ብቁ አመራር በይፋ አመስግነዋቸዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላም በበኩላቸው ለአንድ ሀገር የዲጂታል ሽግግር ስኬት የክህሎት ልማት፤ ፖሊሲወች የህግ ማእቀፋትና ስትራቴጂወችን መቅረጽና ስራ ላይ ማዋል፣ የተቋማት ግንባታን ማከናወን፣ መሰረተ ልማትን በስፋት መዘርጋት፣ የዲጂታል ሲስተም ማልማትና ስራ ላይ ማዋል፣ እነዚሁ ሁሉ አስፈላጊ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የሀገር መሪው ራሱ ለቴክኖሎጂ የቀረበ መረዳትና ፍላጎት (passion) ሲኖረው፣ በስጋቶችና በእድሎቹ ላይ የላቀ መረዳት ይዞ ሲገኝ፣ ከፍ ያለ የቴክኖሎጂ አድናቂና ራሱ የቴክኖሎጂ ሰው ሆኖ ሲገኝ በርግጥም የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ጉዞ ሙሉ በሙሉ የሚሳካ መሆኑን እንድናረጋግጥ አስችሎናል በማለት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጫወቱትን የላቀ አስተማሪ ሚና በመግለጽ አመስግነዋል።"
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች