+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ብሎክቼን ቴክኖሎጂን ከሚያለማ ተቋም ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ።

ስምምነቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ እና የXDMT DATA CENTER ተወካይ ባዝል ባልቢሲ(Basel Balbisi) ፈርመውታል።

ስምምነቱ ብሎክቼንን መሰረት በማድረግ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በትምህርት፣ በአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ እና በግብርና ላይ ሰፊ የትብብር ማዕቀፍ ለመፍጠር ያለመ ነው።

በስምምነቱ ላይ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በመጭው ዘመን የፈጠራዎች ስራዎችን ያለ ብሎክቼይን ማሰብ ብሎም አለማቀፍ ተወዳዳሪነትን ማስቀጠል ከባድ እንደሚሆን በመገንዘብ በዘርፉ እየተሰራ መሆኑን አንስተው እንደ ሀገር ለዲጂታል ቴክኖሎጂ የተሰጠው ትኩረት ይህንንም ያካትታል ብለዋል።

ሚኒስትሩ አያይዘውም ብሎክቼይን ላይ የተመሰረቱ ዳታ ሴንተር ለማልማት የቴክኖሎጂ መድረኮችን በማዳበር እና ተግባራዊ በማድረግ የህዝብ አገልግሎቶችን ለማጠናከር ብሎም ፈጠራን በማጎልበት የሀገሪቱን ስትራቴጂካዊ የእድገት ግቦችን ለመደገፍ ከስምምነቱ ብዙ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

የXDMT DATA CENTER ተወካይ ባዝል ባልቢሲ(Basel Balbisi) በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ድርጅታቸው በብሎክቼን ትልቅ ልምድ ያለው መሆኑን ጠቅሰው ከሚኒስቴሩ ጋር ስራውን ለመስራት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የአካባብ ጥበቃ ስራን በግሪን ቴክኖሎጂ በማገዝ የኢትዮጵያን አረንጓዴ ሌጋሲ ኢኒሼቲቭን በመደገፍ የካርቦን ልቀትን መቀነስ እንዲሁም የካርቦን ክሬዲቶችን በመሸጥ ገንዘብ የማግኘት ስራ በስምምነቱ መሰረት የሚጠበቅ ይሆናል።

የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ አንጻር በትምህርት ሚኒስቴር የተረጋገጠ እና ከብሔራዊ መታወቂያዎች ጋር የተገናኘ ከስህተት ነፃ የሆነ የትምህርት ማስረጃዎችን ለመስጠት ብሎክቼይን እና ስማርት ኮንትራቶችን የሚያገናኝ ደህንነቱ የተጠበቀ መድረክ ይፈጥራል።

የአእምሯዊ ንብረት እና የፈጠራ ባለቤትነት ፍቃድ መድረክ ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር ለአይፒ ምዝገባ ጥበቃ እና ፈቃድ የዲጂታል ደብተር ስርዓት በመዘርጋት ሥራ ፈጣሪዎች እና አዳዲስ ፈጠራዎችን ለመጠበቅ እንዲሁም ለአገር ውስጥ እና ለአለም አቀፍ የንግድ ልውውጥ የአንድ መስኮት ስርዓትን እንዲያገኙ ያግዛል።

Blockchain ላይ የተመሰረተ የግብርና መፍትሔ ከማብጀት አንጻርም የኢትዮጵያን የግብርና ምርት ለመከታተል፣ ለመተንተን እና ለማመቻቸት ሴንሰሮችን፣ ዳታ ትንታኔዎችን እና ብሎክቼይንን በመጠቀም የተቀናጀ ስርዓቱ ለመዘርጋ እንደሚያግዝ ተገልጿል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ