+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በዲጂታል ኢትዮጵያ፣በዘርፉ የስራ እድል ፈጠራ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ውይይቱ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ያለው ጋር የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በሚደረገው ትብብሮች ዙሪያ የተካሄደ ነው።
ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን በተገኘ ልዩ ድጋፍ የመንግስት መሥሪያ ቤቴች የዲጂታይዜሽን ፕሮጀክቶች በተሳካ ሁኔታ መፈጸማቸው እና በዘርፉ የተፈጠሩ የስራ እይሎች እንዲሁም በቀጣይ በሁለቱ ተቋማት በጋራ የሚሰሩ ስራዎች የውይይቱ ዋና ትኩረት ነበር።
በውይይቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በማስተርካርድ ፋውንዴሽን በተሰሩ የፕሮጀክት ስራዎች ዲጂታላይዜሽንን ተግባራዊ በማድረግ የሚሰጡ እገልግሎቶች በማቀላጠፍ እና ውጤታማነትን በማሳደግ ለዜጎች የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራት በእጅጉ እንዳሻሻለው ተናግረውል።
ሚኒስትር አያይዘውም ማስተርካርድ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ለመደገፍ ላበረከቱት አስተዋፅዖ እና ዲጂታል ማካተትን ለማጎልበት እንዲሁም ለወጣት ኢትዮጵያውያን የስራ እድል በመፍጠር ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።
ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በቀጣይም ለኢትዮጵያ ዲጂታል እድገት የሚኖረው አስተዋጽኦ ወሳኝ በመሆኑ ያለው ትብብር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ሚኒስትሩ አንስተዋል።
የማስተርካርድ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ ዳይሬክተር የሆኑት ሚስተር ሳሙኤል ለተሰጣቸው እውቅና ከልብ አድናቆታቸውን ገልጸው ፋውንዴሽኑ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለመደገፍቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።
የጋራ ግቦችን ውጤታማ ለማድረስ ጠንካራ እና ቀጣይነት ያለው የትብብር ሞዴል እንደሚያስፈልግ ያነሱት እቶ ሳሙኤል በኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ መሳካት ከመንግስት እና ባለድርሻ አካላት ጋር የተጠናከረ ትብብር በማድረግ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ኢትዮጵያዊያን ያሳተፈ ጠንካራ እድል መፍጠር እንችላለን ብለን እናምናለን።
ማስተርካርድ ፋውንዴሽን የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን ቅርጽ ላይ በመሳተፍና ፋይናንስ በማድረግ ፣በቬንቸር ሜዳ ስታርታፕ ፕሮግራም ፣በኮቪድ 19 የጤና መረጃ የጥሪ ማዕከል እና በመንግስት ዲጂታል ቢሮ ፕሮጀክቶች ዙርያ ላበረከተው አስተዋጽኦ እና የማስተርካርድ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ያለው ለነበራቸው አበርክቶ በሚኒስትሩ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
ውይይቱ በኢትዮጵያ መንግስት እና በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን መካከል የወደፊቱን የፈጠራ እና የዲጂታል ማጎልበት ትብብርን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንዲሁም
በኢትዮጵያ የዳበረ ዲጂታል ስነ-ምህዳርን ለመፍጠር
መሰረት የሚጥል ነው።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች