+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ኬፒኤምጂ (KPMG) የምስራቅ አፍሪካ በስታርታፕ ስነ-ምህዳር ስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኬፒኤምጂ የምስራቅ አፍሪካ ጋር ለቅድመ-ደረጃ ሥራዎች ማማከር እና የቴክኒክ ድጋፍ ፣ በሥነ-ምህዳር ልማት፣ በፖሊሲ እና በኢንኩቤተር ድጋፍ እና በሕዝብ ፈጠራ ኤጀንሲዎች ተቋማዊ የአቅም ግንባታን ላይ በትብብር ለመስራት መክረዋል።

የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ በኢትዮጵያ የ 10 አመት የልማት እቅድ የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ፣ በቴክኖሎጂ የሚመራ እድገትን እና የስራ እድልን እንደ ሀገር ቅድሚያ የሚሰጣቸውን መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ ለስታርታፕ ትልቅ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ሀገራችን ከህብረቱ ጋር በቀጣይ ተቋማዊ ፈጠራ መሰረቶችን በመገንባት በትብብር ትሰራለች ብለዋል።

የ KPMG ተባባሪ ዳይሬክተር ቫስከን ሲሲያን የ KPMG ን አለምአቀፍ እውቀት ከአካባቢያዊ ግንዛቤ ጋር በማጣመር ስራዎችን፣ የቴክኖሎጂ እድገትን እና አካታች ኢኮኖሚያዊ ለውጥን ላይ በትብብር ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ኬፒኤምጂ የምስራቅ አፍሪካ የጋራ የስራ ቡድን በማቋቋም ወደ ስራ የሚያስገባ የድርጊት መርሃ ግብር እና የሙከራ ፕሮጀክቶችን እንዲዘጋጁ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

ኬፒኤምጂ (KPMG) የምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያ፣ ኬንያን፣ ዩጋንዳን፣ ታንዛኒያ፣ ሩዋንዳ ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ቡሩንዲ፣ ሶማሊያ፣ እና ኤርትራን ያቀፈ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እንደሚሰራ ተገልጿል

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ