+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽን በ“ሰላማዊ ኒውክሌር ቴክኖሎጂ ልማት መርሃ ግብር” ላይ በጋራ ለመስራት መከሩ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽን በ“ሰላማዊ ኒውክሌር ቴክኖሎጂ ልማት መርሃ ግብር” ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችሏቸውን ጉዳዮች በተመለከተ መክረዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የሰላማዊ ኒውክሌር ቴክኖሎጂ ልማት መርሃ ግብሩን በፍጥነት ወደ ተግባር በማስገባት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ልማት አካል ለማድረግ በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በኒውክሌር ቴክኖሎጂ ልማት ላይ ኢንቨስትመንት ለማድረግ የወሰደችው እርምጃ ጊዜውን የዋጀ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ዘርፉ ሀገራችን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ ለምታደርገው ጥረት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ አመልክተዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ቀደም ሲል የጀመራቸውን ሰፋፊ ስራዎች የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽን እንደመነሻ ሊጠቀምባቸው እንደሚገባ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ለዘርፉ ምቹ ስነ-ምህዳር ለመገንባትና አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳንዶካን ደበበ ተቋሙን አደራጅቶ ወደ ስራ ለማስገባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ በአጭር ጊዜ ዘርፈ-ብዙ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡

ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በቅርበት ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ትልቅ ትኩረት የሰጠውን የሰላማዊ ኒውክሌር ቴክኖሎጂ ልማት ግንባታ በፍጥነት በማከናወን የሚፈለገውን ስኬት እውን እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

በምክክሩ ለዘርፉ ስኬት ምቹ ስነ-ምህዳር ለመፍጠር በሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎች፣ የሰው ሀይል ግንባታና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ ያሉ ሀሳቦች ተነስተው የጋራ መግባባት ተደርሶባቸዋል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ