+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ክቡራን ሚኒስትሮች በአዲስ አበባ በተመረጡ ክፍለ ከተማዎች የተሰሩ የልማት ስራዎችን አስመልክቶ የመስክ ምልከታና ሱፐርቪዥን ስራ እያካሄዱ ነው

ከተመረጡት ክፍለ ከተሞች ውስጥ የአደዋ የድል መታሰቢያ ሙዚየም እና የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ የስራ ሀላፊዎች ጋር በመወያየት የተሰሩ ስራዎችን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።

ሱፐርቪዥኑ በአዲስ አበባ የተሰሩ የልማት ስራዎች ያሉበትን ደረጃ በመመልከት የተሻሉትን በሞዴልነት በመውሰድና ያሉ ክፍተቶችን በማሳየት በየዘርፉ የተሻለ ለውጥ ለማምጣት ያለመ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን በቴክኖሎጂ መደገፍና ዲጂታላይዝ ማድረግ ወቅቱ የሚዋጅ ፈጣን የኢኮኖሚ ልማት ለማስመዝገብ መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

እየታዩ ያሉ ስራውች እጅ አመርቂ ቢሆኑም ስራ ሂደት ስለሆነ የማህበረሰባችን ፍላጎት ለማርካትና ተገበውን አገልግሎት ለማሳለጥ የዲጂታል አለሙን መቀላቀልና ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ዋስትና መሆኑን መገንዘብ ይገባል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ በየተቋሙ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ሀገራችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሪፎርሙን ተከትለው አስደናቂ ለውጦች እየተመዘገቡ መምጣታቸውን ማየት መቻላቸውን ተናግረዋል።

ዲጂታል ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ብዙ ቢሆኑም በዲጂታል ክህሎት ላይ እንደሀገር ሰፊ ስራዎችን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የሱፐርቪዥን ቡድኑ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ከጉበኙ በኋላ ጠንካራ ስራዎችን በማበረታታት ያሉ ክፍተቶችን በመጠቆም የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ