+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት ጋር በሀገራዊ የምርምርና ልማት ረቂቅ አዋጅ ላይ መከረ።
ሀገራዊ የምርምርና ልማት አስተዳደር ረቂቅ አዋጁ ላይ ግብዓት ለማሰባሰብ የመንግስት ተቋማት፣ የግል ዘርፉ፣ የምርምር ተቋማት፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ያማከለ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ (ፒ ኤች ዲ) የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማት ሥራዎች ለዓለማችን አንገብጋቢ ችግር መፍቻ ቁልፍ መሳሪያ በመሆናቸው በ2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን እንዲሁም በአፍሪካ 2063 አጀንዳን ለማሳካት ወሳኝ ድርሻ እንዳለው አስገንዝበዋል።
ምርምርና ልማት፣ ፈጠራ፣ የቴክኖሎጂ ልማት እና ሽግግር በአንድ አገር በእውቀት ላይ የተመሰረተና ሁለተንተናዊ እድገት ለማምጣትና በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት የተለያዩ አዋጆችን፣ ፖሊሲዎችን እና ስትራቴጂዎችን ቀርጾ ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ፒ ኤች ዲ) ለምርምርና ልማት ሥራዎች የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ ከ25,000 እስከ 5 ሚሊዮን ብር ማድረስ መቻሉ፣ የምርምር ተቋማት አቅም ማደጉ፣ የተመራማሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩ፣የግል ዘርፉ ተሳትፎ እያደገ መምጣቱ፣ በእውቀት ላይ የተመሰረት ኢኮኖሚ ግንባታ መሰረት መጣል መጀመሩ አንስተዋል።
ምርምር የሁሉም መሰረት ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በሀገር ደረጃ ዘርፉን በይበልጥ ውጤታማ ለማድረግና ለመምራት ያስችል ዘንድ ከተለያዩ ሀገራት የልምድ ልውውጥና ተሞክሮዎችን የመቀመር ስራ በማከናወን አዳዲስ መዋቅሮችንና ተጨማሪ አስራሮችን የመዘርጋት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የሀገራችን የኢኮኖሚ እድገት እንዲበለፅግና እቅዳችን እንዲሳካ በምርምር ዘርፉ ላይ ያሉ መሰናክሎች እንዲቀረፉ በረቂቅ አዋጁ ላይ የሚደረገው የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተሳታፊዎች ጠይቀዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች