+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአልጄሪያ የዕውቀት፣ ኢኮኖሚ፣ ስታርታፕ እና ማይክሮ ኢንተርፕራይዝ ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

ከ3ኛው የአፍሪካ ስታርታፕ ጉባኤ እና አውደ-ርዕይ ጎን ለጎን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ከአልጄሪያ የዕውቀት ኢኮኖሚ፣ ስታርታፕ እና ማይክሮ ኢንተርፕራይዝ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጋር በኢኖቬሽን፣ በቴክኖሎጂ፣ በምርምር ፣ በሰው ኃይል አቅም ግንባታ ላይ በመምከር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ የስታርታፕ ስነምህዳር ላይ ሰፋፊ ስራዎችን በመስራት ሁሉም ዜጎች ከዘርፉ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ስርዓት ግንባታ ላይ እየሰራች መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አክለውም ዘርፉ ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ወሳኝ በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች፣ ባለሀብቶች፣ ኢንቨስተሮች እና ከአለም አቀፍ ሀገሮች ጋር በትብብር እየሰራ ቢሆንም በቀጣይ ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ዝግጁ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ የተመራው ቡድን በአልጄሪያ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ስታርታፕ ኮንፍረንስ የሚኒስትሮች መድረክ ላይ በመሳተፍ በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ የሀገራችንን አቋም በማንፀባረቅ ላይ ይገኛል፡፡

በኮንፈረንሱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የትምህርት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኮሚሽነር፣ የአፍሪካ ሲቪል ማህበረሰብ ተወካይ፣ የግል ዘርፍ ተወካዮች፣ ከሁሉም አፍሪካ ሃገራት ሚኒስትሮች እና የሀገራት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ